አባይ ሚዲያ የካቲት 30፤2012

በምዕራብ ኦሮሚያ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም እየተወሰደ ባለው እርምጃ፣ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የኦነግ ሸኔ አባላት እጃቸውን እየሰጡ እና እየተያዙ መሆኑን ተገለጸ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ አካባቢ ለውጥ መጣ ከተባለ ወዲህ የተረጋጋ ጸጥታ አለመኖሩንና የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ ብዙ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ከፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ምዕራብ ክፍል ህገወጥ ድርጊት እየፈጸሙ ናቸው ባላቸው የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ረዘም ያሉ ግዜያት ማስቆጠሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል በንጹሃን ዜጎች፣ በፖሊስ አባላትና በውጭ ሃገራት ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸም ከህገወት ድርጊቶቹ መካከል  ይጠቀሳሉ።

በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በርከት ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽሙ መቆየታቸውም ተገልጿል እየተወሰደ ያለው እርምጃ ከእስካሁኖቹ የጠነከረ እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ገልጿል ከዚህ ጋር ተያይዞም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ እንደገለጹት እራሳቸውን ኦነግ ሸኔ ብለው ከሚጠሩት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በክልሉ ፖሊስና የጸጥታ አካላት በተኩስ ልውውጥ ህይወታቸው ያለፉ እንዳሉ ሁሉ በእጅ የተያዙ እንዳሉም ገልጸዋል።

አካባቢውን የማጥራት ስራ በሰፊው እየተሰራ እንደሆነና መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነም ኃላፊው አስረድተዋል አቶ ጌታቸው ጥፋት ሲፈጽሙ የነበሩ ያሏዋቸውን ኃይሎች መችና እንዴት እንደተያዙ አጠቃላይ ቁጥራቸውን ጨምሮ በቅርቡ በፖሊስና የጸጥታ አካላት መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸው አስቀድሞ ግን ለስራው ፍጥነትና ለመረጃ አያያዝ አስፈላጊነት ያመች ዘንድ ጥልቅ መረጃዎችን ለመያዝ እንደሚገደዱ አስረድተዋል።