አባይ ሚዲያ መጋቢት 2፤2012

የእንግሊዟ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተያዙ ሚኒስትሯ ናዲን ዶሪስ በዩኬ በቫይረሱ የተያዙ የመጀመሪያዋ የሕዝብ እንደራሴ ሲሆኑ ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ አንደወሰዱና ራሳቸውንም ከሌሎች አግልለው መቀመጣቸውን ተናግረዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ፣ ናዲን ዶሪስ ያገኟቸው ሰዎች በአጠቃላይ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል በተመሳሳይ የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውና እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸው ተገልጧል።