አባይ ሚዲያ መጋቢት 2፤2012

የታጋች ተማሪዎች ቤተሰብ መንግስት ልጆቻችን “ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበለን” ሲሉ ጠየቁ ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ በነበሩበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘለት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ከታገቱ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ ጀምሮ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመልሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል ትላንት ደግሞ ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ባህር ዳር ተገኝተው ነበር።

ወይዘሮ እንዳለች ይመር ሴት ልጃቸው እስታሉ ቸኮለ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንደኛዋ እንደሆነች ይናገራሉ ከመንግሥት አካል ምላሽ ብንጠብቅ ብንጠብቅ ምንም የለም፤ ያሉት ወይዘሮ እንዳለች እስቲ አሁን መልስ ካገኘን ብለን ነው ባህርዳር የመጣነው” ብለዋል።

” በቃ ወይም ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን፤ እኛም እርማችንን አውጥተን አርፈን እንቀመጥ ሲሉም እንባ እየተናነቃቸው ጠይቀዋል” ሌላኛው ልጃቸው እንደታገተችባቸው የሚገልጹት መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የታገተች ልጃቸውን በተመለከተ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ድረስ መሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ከተመለስን በኋላም በአጭር ጊዜ መፍትሔ ይመጣል ብለን ነበር ያሉት መሪጌታ የኔነህ 35 ቀን ሆነን ውጤት ባለመገኘቱ ዛሬ ክልል መጥተናል” ብለዋል በባህር ዳር ቆይታቸውም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ እና ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ቢሞክሩም በተለያየ ምክንያት ኃላፊዎችን ሳያገኙ መቅረታቸውንም ገልጸዋል።

የእህቷን ጉዳይ ለመከታተል አዲስ አበባ የነበረችው የታጋች ተማሪ እህት ፍቅርዓለም ቸኮለ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ እንደምትገኝና ከሰሙም ከወር በላይ እንደሆነው ወይዘሮ እንዳለች ይመር ለቢቢሲ ገልጸዋል የእስታሉ ታላቅ እህቷ ስትሆን ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ሁለት ዓመት እንደሆናትና አዲስ አበባም ስራ እየፈለገች እንደነበር ተናግረዋል።”

የታገተችዋ ተማሪ እህት መሆኗን የሚያስረዳ ማስረጃ አቅርባ መጋቢት ዘጠኝ እንደምትለቀቅ ስለተነገራቸው ይህንኑ በጉጉት እየጠበቁ መሆኑንም አስታውቀዋል መሪጌታ የኔነህ በበኩላቸው ” 95 ቀን እያለቀስን ነው፤ አዝመራ አልተሰበሰበም፤ እናቶችም በአእምሮ እየተጎዱ ነው ብለዋል አክለውም ” መንግስት በአፋጣኝ እናቶች አእምሯቸው የበለጠ ሳይዛባ እንዲስተካከሉ ቶሎ ከሁለት አንዱን ቢለይልን ነው የምፈልገው” ብለዋል።

ከሰሞኑ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ከእገታው ጋር ተያይዞ ፓርቲያቸው ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የተለያየ መግለጫ በመሰጠቱ የህብረተሰቡን አእምሮ ካለመያዙም በላይ አንዳንዱ መረጃ ተፋልሶ ያለበት ነበር ብለዋል።