አባይ ሚዲያ መጋቢት 07፤2012

የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጉትጎታ የወሰዷቸውና ያለ ሥራ ያስቀመጧቸው መሬቶች ሊለዩ ነው የመሬት ልማት ባንክ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ በስሯ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጉትጎታ የወሰዷቸውንና ያስቀመጧቸውን መሬቶች እንደሚለይ ሰሞኑን ለዚሁ አላማ የተቋቋመው መስሪያ ቤት ተናግሮ ነበር፡፡

አዲስ አበባ የሀገሪቷ ዋና ከተማ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በዙሪያዋ ወደሚገኙ ትንንሽ ከተሞች እየተለጠጠች መሄዷ ሲነገር ቆይቷል የአዲስ አበባን የመሬትና ሊዝ ሁኔታን ይወስናል የተባለው ማስተር ፕላን ከዛሬ ነገ ስራ ላይ ይውላል በሚል ምክክሮች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ሰሞኑን የመሬት ልማት ባንክ ኮርፖሬሽን ያለልማት የተቀመጡ የመንግስት መሬቶችን መዝግቤ እሰበስባለው ለሚገባውም ስራ አውለዋለው በሚል የፕሮጀክት ስራ መጀመሩን ተናግሯል፡፡

ለመሆኑ ይህ ጉዳይ ወሰኗና ድንበሯ በየጊዜው ውዝግብ ለሚነሳበት ከተማ እንዴት ይፈፀማል፤ይዞታዎቹ ሲለዩስ ገና በሰነድ ደረጃ ካለው ማስተር ፕላን ጋር እንዴት ይጣጣማል ለሚለው የመሬት ልማት ባንክ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክሯ እንደገለጹት ይህ ስራ ሲከወን በእንጥልጥል ላይ ያለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ እንዴት አብሮ ይጓዛል የሚለውን እየሰራንበት ነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር አልደረስንም አሁን የፌደራል ይዞታዎችን ነው እየመረጥን የምናወጣው ብለዋል፡፡

የፌደራል ተቋማት ለተለያዩ አገልግሎቶች የያዟቸው ይዞታዎች አሉ ፤ እነሱም ለቢሮ ፣ ህንፃ ለመገንባት ፣ ሰርቪስ ለመስጠትና ለፓርክ የተያዙ ናቸው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ ከማስተር ፕላኑ ጋርም የሚጣጣምበትን መንገድ በጊዜ ሂደት ለማለማመድ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

በመንግስት ተቋማት የተያዙ የሊዝ መሬቶችን የመለየቱን ስራ ለማከናወን በተለይ በፕሮጀክት ደረጃ የሚጀመረው በአዲስ አበባ በመሆኑ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩንም ዋና ዳይሬክተሯ ሌንሳ ይናገራሉ፡፡

ኮርፖሬሽኑ እንደተናገረው በኢትዮጵያ በመንግስት ተቋማት ስር የሚገኙ የተለዩ 384 ቁራሽ መሬቶች እንዲሁም 106.72 ኪሎሜትር ካሬ ስፋት የሚገመቱ ይዞታዎች መኖራቸውን ገልጿል ከእነዚህም ውስጥ በፕሮጀክቱ መጀመሪያ 384 ይዞታዎችን በ 6 ወራት ውስጥ ለማጣራትና በስራ ላይ ያልዋሉትን ለመለየት እንደታሰበ ተነግሯል፡፡