አባይ ሚዲያ መጋቢት 07፤2012

ባንኮች አንድ ዶላር በ33 ብር እየሸጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡

ዛሬ መጋቢት 07/2012 በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች አንድ ዶላር በ33 ብር አካባቢ እየሸጡ መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋግጫለሁ ስትል ዘግባለች።

ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸርም የአንድ በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ዶላር ወደ 42 ብር ገደማ እየተሸጠ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል።

በተመሳሳይ አንድ ፓውንድ በሁሉም ባንኮች እስከ 39 ብር ከ75 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን አንድ ዩሮ ደግሞ 37 ብር አካባቢ በመሸጥ ላይ ነው በተጨማሪ አንድ የኩዌት ዲናር በ102 ነጥብ 7ብር እየተሸጠ ይገኛል።