አባይ ሚዲያ መጋቢት 07፤2012

ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከቀዳሚዎቹ አንዷ መሆኗ ተገለጸ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካ ፤ ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከፍተኛ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ፍሰት የሚስተዋልባቸው ሀገራት መሆናቸውን አንድ ሪፖርት አመልክቷል።

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ታዋቂ የአሜሪካ የምርምር ቡድን የሆነው ብሮኪንግስ ኢንስቲትዩት ሀገራቱን ይፋ ባደረገበት አዲስ ሪፖርት ናይጄሪያ ፤ ደቡብ አፍሪካ ፤ ኢትዮጵያና ኮንጎ በአፍሪካ 50 በመቶ ግልጽ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን ያስተናግዳሉ ብሏል።

ሪፖርቱ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰት ለአህጉሪቱ አዲስ አለመሆኑን የገለፀ ሲሆን እንደ አውሮፖውያኑ ከ1980 እስከ 2018 ባሉት አመታት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት 2 ትሪሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና የልማት ድጋፎች መሳባቸውን ገልጿል።

እንደ አለመታደል ሆኖ ከተቀበሉት ገንዘብ ውስጥ ከ 1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነው በሕገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰቶች ከአፍሪካ ወጪ ሆኗል ተብሏል።