አባይ ሚዲያ መጋቢት 8፤2012

ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ አላስፈላጊ ስጋት ውስጥ ከመግባት ይልቅ የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመተግበር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።

ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ ሊያደርገው በሚገባው ጥንቃቄ ዙሪያ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታቸውም፥ ህብረተሰቡ ቫይረሱ ከአንዱ ወደ ሌላው በቀላሉ እንዳይተላለፍ ከእጅ ንክኪ እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

አቶ ሽመልስ አክለውም፥ በጤና ባለሙያዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ መልእክቶችን እና ምክሮችን መተግበር፣ እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለመደው መንገድ ተቃቅፎ ሰላም ከመለዋወጥ መቆጠብ ይጠበቅብናልም ብለዋል።