አባይ ሚዲያ መጋቢት 8፤2012

በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአገር ውስጥ በረራ የአየር ጠባዩ በመስተካከሉ በረራው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በረራው በመቋረጡ መንገደኞች መጉላላት አጋጥሟቸዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በረራውን ያስተጓጎለው የአየር ንብረት የተስተካከለ በመሆኑ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመመደብ መጉላላት ያጋጠማቸውን ደንበኞቹን ለማስተናገድ እንደሚሰራ አየር መንገዱ ገልጿል በዚሁ መሰረት ከትናንት ጀምሮ በረራውን እንደቀጠለ አስታውቋል።

ወደ ደሴ የሚደረገው በረራ በአካባቢው በተከሰተው የአየር ጠባይ ለውጥ እንደተስካከለ የበረራውን መጀመር አየር መንገዱ በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑን አመልክቷል።