አባይ ሚዲያ መጋቢት 9፤2012

ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 እስከ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንደሚዘጉ ተገለጸ።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በከፊል እንደሚዘጉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ቀጠሮ ያላቸው ሐሙስ እና አርብ ቀጠሮ እንደሚሸጋሸግላቸው በመግለጫው ተገልጿል ከሰኞ ጀምሮ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እና የ992 የመዝገብ ቀጠሯቸውን ማየት ይችላሉ።

ወይም የቀጠሮ ቀናት በየፍርድ ቤቶች ይለጠፋሉ ተብሏል አዲስ መዝገብ መክፈት ወይም አዲስ ክስ መመስረት ለሚፈልጉ ሰዎች ወይም ተቋማት ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እንደማይቻልም ወይዘሮ መዓዛ ተናግረዋል።

ልዩ ወይም አስቸኳይ እና ከአገር ደህንነት ጋር በተገናኘ በልዩ መልኩ ተረኛ ዳኞች ፋይል ሊከፍቱ ይችላሉ ተብሏል ይህ በእንዲህ እንዳለ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ሰራዊቱ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል አደም መሀመድ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ በሀገርና በውጭ በርካታ ግዳጆችን አየተወጣ ነው።

በመሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ እንደይጠቃ ሰራዊቱ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል ሰራዊቱ የተጣለበትን ድርብ ሀላፊነት ለመወጣትም ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆን አለበት ነው ያሉት።

ሰራዊቱ በአንድ ካምፕ ሰብሰብ ብሎ የሚቀመጥ በመሆኑና ለግዳጅ ከቦታ ቦታም ስለሚንቀሳቀስ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብለዋል የሰራዊቱ አባላት ላልተወሰነ ጊዜ ከካምፕ ውጭ ያለ ስራ መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው መክረዋል።

በሽታውንም ለመከላከል በሁሉም ካምፖች በቂ የሆነ የውሃ አቅርቦት እንዲኖርም ጥረት እንደሚደረግ ነው ያስረዱት በሌላ በኩል አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ [ኮቪድ-19] ክፉኛ ከተጠቁት አገራት መካከል ቀዳሚዋ በሆነችው ጣሊያን ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡

በወረርሽኙ የሞቱት ሁለቱም ሰዎች ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የነበረ ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን አንደኛው ለረጅም ዓመታት ጣሊያን ውስጥ የኖሩ መሆናቸውም ታውቋል፡፡