አባይ ሚዲያ መጋቢት 14፤2012

በኦሮሞ ብሔረሰብ በኮሮና የተጠረጠረው ግለሰብ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ካሊድ ሙስጠፋ እንዳስታወቁት የ27 አመት እድሜ ያለው ወጣት መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከሳውዲ አረቢያ በመግባቱ በኮረና ቫይረስ ተጥርጥሮ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በከሚሴ ሆስፒታል በተደረገለት ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል ፡፡

ሃላፊው አያይዘውም ከዛሬ ጀምሮ የከሚሴ ጤና ጣቢያ ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ማቆያ እንዲሆን በመደረጉ ለህሙማን የከሚሴ ሆስፒታል መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ መረጃ የቫይረሱ ጥርጣሬ ታይቶባቸው በባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ምርመራ ሲደረግላቸው የነበሩት ሴት ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡