አባይ ሚዲያ መጋቢት 14፤2012

በግድቡ ድርድር ሂደት ኢትዮጵያን ያስቸገራት ነገር ግብጽ በየጊዜው የምታደርገው የአቋም መለዋወጥ እንደሆነ ተገለጸbድርድሩ መቋጫ ባላገኘው የኢትዮጵያ የግብጽና የሱዳን ድርድር አነጋጋሪቱን ቀጥሏል፡፡

በተለይም ግብጽ የተለያዩ ሀገራትን  ድጋፍ ለማግኘት ደፋ ቀና ከማለት አልተቆጠበችምbጊዜው ከረፈደ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን ምሁራንና ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን የባለቤትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብት ለአለም ለመሳየት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ  የግብፆች ችግር አቋማቸውን መቀያየር ነው ያሉ ሲሆን ለምሳሌ ካርቱም ላይ ተሰብስበው የተስማሙበትን ነገር ካይሮ ላይ ሲቀጥል ያንን ገልብጠው እንዳልተስማሙ ሆነው ይገኛሉ፤ ወይም ሌላ አዲስ ፍላጎት ይዘው ይመጣሉ። ይህ ለተደራዳሪዎች፤ በተለይ ለኢትዮጵያውያን ከባድ ራስ ምታት ሆኖ ነበር በማለት ይገልጻሉ።

የህዳሴው ግድብ በሱዳን መውጫ አካባቢ እየተገነባ ያለ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር ተስፋየ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2011 ይህን ግድብ በራሷ መሬት ላይ በራሷ ገንዘብ ለመገንባት የወሰነችው ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ላይ የሚገነባ ግድብ ሁሉም አገራት ያልተስማሙበት ከሆነ የዓለም ባንክ አይረዳም ሲሉ ያስረዳሉ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ምርጫ ስላልነበረው በራሱ ህዝብ፤ ጉሊት ከምትቸረችረው ምስኪን ነጋዴ እስከ ከፍተኛ ባለሃብት ድረስ ያሉት ህዝቦች አዋጥተው ቦንድ ገዝተው ለመገንባት ተገድዷል።

በ1959 ዓ.ም ደግሞ ኢትዮጵያን ሳያካትቱ ሱዳን እና ግብፅ ስምምነት አደረጉ የሚሉት ምሁሩ 11 የተፋሰስ አገሮች ያሉ ቢሆንም ውሀውን ለግብፅ 75 በመቶ ለሱዳን 25 በመቶ በሚል ሁለቱ ብቻ ተስማምተውበታል በማለት ይኮንናሉ።

ግብፅ “ድርሻዬ ነው፤ ታሪካዊ መብቴ እና አይነኬ ነው” ትላለች። ነገር ግን፤ በቅኝ ግዛት ዘመን ላይ የነበሩትን ስምምነቶች ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም የተፋሰስ አገሮች እነታንዛኒያ እነኬኒያ በሙሉ የሚቀበሏቸው አይደሉም ሲሉም አክለዋል።

ፕሮፌሰር ተስፋየ የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት የኔሬሬ ዶክትሪን የሚባል ነገር አለ። እርሳቸው “በቅኝ ግዛት ዘመን የተካሄዱ ስምምነቶች በሙሉ ተቀባይነት የላቸውም” ብለዋል። ኢትዮጵያም የኔሬሬ ዶክትሪን ተቀባይ ናት። ኢትዮጵያ የ1959ኙን ስምምነት በዚያ ዘመን “አልቀበልም፤ እኔ አልታሰተፍኩበትም።” እያለች ነበር በማለት አውስተዋል።

ግብፆች ግን በዚያ ወቅት ኢትዮጵያ ትቃወመው የነበረውን ስምምነት “ዋና መሰረታችን ነው” ብለው እርሱን ማዕከል አድርገው መንቀሳቀሳቸው ትልቅ ችግር ሆኗል። ስለዚህ ተደራዳሪዎቹ አንድ ቦታ ይሰባሰባሉ፤ ግን አይስማሙም ሲሉ የድርድሩን እንቅፋት ያመለክታሉ።