አባይ ሚዲያ መጋቢት 15፤2012

የውንብድና ወንጀል የፈፀሙት 3 ተከሳሾች የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አካባቢ ከምሽቱ 4፡00 ልዩ ቦታው ናዝራዊ ሆቴል አካባቢ ሶስት ግለሰቦች ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በመሆን በሚኒባስ ስርቆት ፈፅመዋል፡፡

ተከሳሾቹ ሁለት ግለሰቦችን በማፈን የ20 ሺ ብር እና የ16ሺ ብር ስልክ ከወሰዱ በኋላ አንደኛው ግለሰብ በከፍተኛ ሁኔታ በመደብደቡ ህይወቱ ሲያልፍ አብራው የነበረችው ግለሰብ ለምስክርነት መቅረብ ችላለች፡፡

በአቃቢ ህግ ክስ አማካኝነት የተያዙት ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምንም ያሉ ሲሆን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ችሎት መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም 3ቱንም ተከሳሾች እያንዳንዳቸውን በእድሜ ልክ እሰራት እንዲቀጡ ወስናል፡፡