አባይ ሚዲያ መጋቢት 15፤2012

እስፕሬይ እና የአልኮል ሽቶ ቀላቅለው አልኮል ሲሸጡ የነበሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አልኮልና እስፕሬይ ከአልኮል ሽቶ ጋር ቀይጠው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ አለሙ፣ በግለሰቦቹ ላይ የተጀመረው የምርመራ ሂደት እንደቀጠለ ገልፀው፣ በየወቅቱ የሚከሰቱ ችግሮችን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ከህዝብ ደህንነት ይልቅ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ህገ-ወጥ ድርጊታቸውን ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡