አባይ ሚዲያ መጋቢት 19፤2012

ሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል መንግስት ትእዛዝ ተዘጋ ከ70 አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ የተቋቋመው እና በኋላም  ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዞር የተወሰነው የሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ትእዛዝ ባሳለፍነው ሃሙስ መጋቢት 17 ቀን 2012 አ.ም መዘጋቱን ሪዞርቱ አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ዲንቁ ደያስ ከአሜሪካ እንደገለጹት ለጊዜው ሪዞርቱ ለምን እንደተዘጋ አላውቅም ፡፡እኔ የማምነው ግን ያለአግባብ ግፍ እየተፈጸመብኝ እንደሆነ ነው ያሉ ሲሆን የሪዞርቱ አመራሮች ታስረው እንደነበርም አቶ ድንቁ አረጋግጠዋል፡፡

ከእሱ ጋር ስብሰባ ነበረን ስብሰባውን ትቶ ወደ አሜሪካ ሄዷል በሚል ምክንያት እንደያዟቸው ሰምቻለሁ ሲሉም በሪዞርቱ የሚሰሩ የስራ ሀላፊ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ከሀገር ሸሽተው ወጥተዋል መባሉን ያስተባበሉት አቶ ዲንቁ ስራ ስላለኝ ነው የወጣሁት ፣ ለመመለስ ደግሞ  ሁኔታው አላስቻለኝም እንጂ መመነሴ አይቀርም ማንንም ፈርቼ አልቀርም ብለዋል፡፡

የሪዞርቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አብዮት ተመስገን በበኩላቸው ሪዞርቱ በማን ትእዛዝ እንደተዘጋ የምናውቀው ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጊዮን ሆቴልን ወደ ግል ለማዞር ወጥቶ በነበረው ጨረታ አሸንፈው የነበሩት አቶ ዲንቁ እስካሁን ግን ውል አልፈረሙም ፡፡ያስያዝኩትን 68 ሚሊዮን ብር አልመለሱልኝም ወይም ሆቴሉን አላስረከቡኝም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሪዞርቱ የሚሰሩ አንድ ስራ ሃላፊ ሆቴሉ እንዲዘጋ የተደረገው በፖለቲካዊ ያለመስማማት ነው ሃላፊው እንደገለጹት በሆቴሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ይሰበሰባሉ የሚለው ምክንያት ለመዘጋቱ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡

ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በ40 ሚሊዮን ብር በነጻ እያሰራሁ ነው ያሉት አቶ ድንቁ መንግስት ሊሸልመኝ ሲገባ መንገላታቴ አግባብ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የገበሬን መሬት ነክተሃል የሚሉትም እኔ ሪዞርቱን የገዛሁት ከመንግስት ሲሆን መንግስት በሰጠኝ ልክ ብቻ ነው ያለማሁት ምንም አይነት የግብር እዳም ሆነ ሌላ ወንጀል የለብኝም ሲሉ አቶ ዲንቁ ተናግረዋል ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው፡፡