አባይ ሚዲያ መጋቢት 19፤2012

የግል ድርጅቶች የሰራተኞቻቸውን ጡረታ በተገቢው መንገድ እያስገቡ አይደለም  ተባለ የግል ድርጅቶች የሰራተኞቻቸውን የማህበራዊ ዋስትና ገንዘብ በተገቢው መንገድ እየከፈሉ እንዳልሆነ የግል ድርጅቶች የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

እንዲህ ዓይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከሰራተኞቻቸው  በሚመጣ ጥቆማ መሰረት ኤጀንሲው ለመያዝና ህጋዊ ርምጃ ለመውሰድ አንደሚንቀሳቀስ የኤጀንሲው የአበል ክፍያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቅዱስ ሀጎስ ተናግረዋል፡፡

ኤጀነሲው በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጥቆማዎቹ ከመጡ በኋላ ድርጅቱ እስካሁን ያሉትን የክፍያ ማስረጃ  እንዲያቀርብ የሚጠይቅ ከፍ ሲልም የሚያስገድድ ሲሆን ፤በመቀጠል ትክክል መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ በቅድሚያ የክፍያ ማሳወቂያ  ጊዜ አምስት ቀናት የሚሰጡት እንደሚሆን አሰታውቀዋል፡፡