አባይ ሚዲያ መጋቢት 21፤2012

የከተማ አስተዳደሩ ከኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከል ጋር የተላለፉ ውሳኔዎችን ባላከበሩ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር በመተባበር ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ 16 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሺሻ ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጋቸውን የከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ትዝብት አባቡ እንደገለፁት 20 ጭፈራ ቤቶችና 19 ከረንቡላ ቤቶችን ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲዘጉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ትራንስፖርት ላይም ከትራፊክ ፖሊስና መንገድ ትራንስፖርት ጋር በመሆን 12 ሰው የሚጭኑ ሚኒባሶች 6 ሰው እንዲጭኑና ባጃጆች ከሁለት ሰው በላይ እንዳይጭኑ መደረጉን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።