አባይ ሚዲያ መጋቢት 22፤2012

የፕሮቴስታንት እምነት መምህሩና በመልካም ወጣት ፕሮጀክት የሚታወቀው አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በሀዋሳ ከተማ ጥቃት እና እንግልት ደረሰበት የአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እናት የሆኑት ወ/ሮ ትግስት ካሳ ለአባይ ሚዲያ እንደተናገሩት አገልጋይ ዮናታን ለ4 አመታት እየኖረ በሚገኝበት ሀዋሳ ከተማ በዛሬው እለት ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በከተማው ለሚካሄደው የጸረ ተህዋስያን ርጭት የበኩሉን ለማበርከት ለመልካም ወጣት ፕሮጀክት ህንጻ ማሰሪያ የተገዛውን መኪና ለርጭት እንዲውል ነዳጅ በመሙላት ለከተማው ጤና ቢሮ አስረክቦ እየተመለሰ ባለበት ወቅት አንድ የጸጥታ አስከባሪዎች አስቁመው እንደሰደበው እና መኪናው በድንጋይ እንደተደበደበ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ትግስት እንደገለጹት ከዚህም ቀደም እንደዚህ አይነት መሰል ድርጊቶች ይፈጸሙበት እንደነበር ገልጸው ከቀናት በፊትም አገልጋይ ዮናታንን ነው የምንፈልገው በሚል የካሜራ ባለሙያዎቹ ከቢሮ ወደ ቤተክርስቲያን እያቀኑ በነበረበት ወቅት ታስረው እንደነበር እና በኋላም ላይ አገልጋይ ዮናታን ባደረገው ጥረት መፈታታቸውን ገልጸዋል በጉዳዩ ላይ የጠራ መረጃ ለማግኘት አባይ ሚዲያ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉን አነጋግሮታል፡፡