አባይ ሚዲያ መጋቢት 24፤2012

የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው የሚያዚያ ወር ክፍያን እንዲከፍሉ  ማስታወቂያ  እያወጡ መሆኑን የተማሪዎች ወላጆች ለአባይ ሚዲያ ተናግረዋል መንግስት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ መወሰኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ነገር ግን አንዳንድ  የግል ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው የሚያዚያ ወር ክፍያን እንዲከፍሉ በማስታወቂያ ጭምር ጥሪ በማድረግ ላይ እንደሆኑ እየታየ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የእንተሳሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል የትምህርት ሚ/ር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ በበኩላቸው ተግባሩ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው ፤ት/ቤቶቹ የመምህራን ክፍያና የቤት ኪራይ ወጪ ስለሚኖርባቸው ችግሩ ከተባባሰ መንግስት ምን መደረግ አለበት የሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚደረግ  ተናግረዋል ፡፡

ለአሁኑ ግን ት/ቤቶቹ በዚህ ተግባር የሚቀጥሉ ከሆነ መንግስት ጣልቃ  እንደሚገባ ገልጸዋል ምን አልባትም አሉ  ሚንስትር ዴኤታው ይህ ችግር እንደ አገር ከገጠመን ቀናቶች ብቻ የተቆጠሩ ሲሆን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ መግባት ተቋሞቹንም ትዝብት ውስጥ የሚጥልና በነገ መልካም ስማቸው ላይ ጥላሸትን የሚቀባ  ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም  ት/ቤቶቹ ለተማሪዎቻቸውና ለወላጆቻው  አሰፈላጊውን  ትብብር ቢያደርጉና አገራዊ ሃላፊነታቸውን ቢወጡ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አባይ ሚዲያ ያነጋገራቸው መምህራን የትምህርት ቤቶቹ ተግባር ተገቢ አለመሆኑን እና  በእለት ተእለት የስራ ገቢያቸው  ዋጋ ከፍለው ልጆቻቸውን ለሚያስተምሩ ወላጆች ችግሩ እነሱንም ከቤት አሰቀርቷልና ድርጊቱ ከባድ  ይሆናል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አንድ አንድ የግል ት/ቤቶች በኢንተርኔት ትምህርት በመስጠት ተማሪዎቻቸውን እያገዙና በተመሳሳይም የተለያዩ ቁሳቁሶችን፤ህንጻዎችንና የገነዘብ ድጋፎችን ለተቋቋመው ኮሚቴ እያበረከቱ ስለሆነ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ያነጋገርናቸው  ወላጆችም በዚህ አለም ጭንቅ ውሰጥ በገባችበት ወቅት  ወላጆችን ክፈሉ ብሎ ማስጨነቁ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው  አቅሙ ለሌላቸው ት/ቤቶችም መንግሰት አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርግ  የተሻለ ነው ብለዋል፡፡