አባይ ሚዲያ መጋቢት 26፤2012

3 ግለሰቦች የመድሃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች ነን በማለት በማጭበርበር ገንዘብ ለመቀበል ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን ሲፈፅሙ የተያዙት መጋቢት 23/2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በአንድ ግለሰብ ምግብ ቤት ውስጥ ነው፡፡

የማጭበርበር ወንጀል የተፈጸመበት ሆቴል ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ዘይነብ ሸምሱን ስለወንጀሉ አፈፃፀም  በሰጡት ምላሽ ተጠርጣሪዎቹ ከልደታ ክፍለ ከተማ የመድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን እንደመጡ እንደገለጹላቸው ጠቅሰዋል፡፡

በመቀጠልም ምግብ ቤቱ ፅዳት ይጎድለዋል፣ በዚህ ፅዳቱ ባልተጠበቀ ቤት እንዴት ትሰራላችሁ? ስለዚህ እናሽገዋለን፤ወይም በገንዘብ እንደራደር ሲሏቸው የግል ተበዳይም በመጠራጠር ወደቤታቸው በመግባት ለሚመለከተው አካል ደውለው ከተቋሙ ያልተላኩ መሆኑን በማረጋገጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡