አባይ ሚዲያ መጋቢት 26፤2012

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 89 ሰዎች ውስጥ ሦስት ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት አገግመዋል ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሦስቱም ግለሰቦች የውጭ አገሮች ጉዞ ታሪክ ያላቸውና ሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው።

”የመጀመሪያው ግለሰብ የ29 ዓመት ወንድ ሲሆን መጋቢት 10 ቀን ከዱባይ የመጣና በበሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው ነው” ብለዋል ሁለተኛው የ34 ዓመት ወንድ መጋቢት 23 ከዱባይ የመጣና በማቆያ የነበረና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው መሆኑ ታውቋል ሶስተኛዋ የ35 ዓመት ሴት በመጋቢት 25 ከስውዲን የመጣችና በማቆያ የነበረች መሆኗን ገልጸዋል ዛሬ ከቫይረሱ ያገገሙትን የ85 አዛውንት ጨምሮ በድምሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበበና በአዳማ 641 ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገላቸው መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህም 510 ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ጠቁመዋል በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በከተማዋ እንቅስቃሴዎች ሊገደቡ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የከተማዋ የታክሲ አገልግሎትን ጨምሮ መደበኛ እንቅስቃሴ እንደማይቆም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል ኢንጂነር ታከለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ታክሲዎች ትርፍ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፈው ሳምንት የተደረገው የፀረ ተዋህስያን ኬሚካል ርጭት በተከታታይ እንደሚደረግ ጠቁመው፥ አስተዳደሩ ከአዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ወደ ማምረት እየገባ መሆኑንም አስረድተዋል አሁን ላይም በሸማች ማህበራት አማካኝነት ከ200 ሺህ በላይ የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎችን የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በማህበራቱ በኩል እንደሚያቀርብ ያስታወቁት ከንቲባው የምርት እጥረት እንዳይከሰት የከተማ አስተዳደሩ 600 ሚሊዮን ብር በመመደብ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን ወደ ሸማች ሱቆች እያስገባ ይገኛል ብለዋል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልም በመዲናዋ ከ30 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተሰማሩ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ መሠብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል በቀጣይም ድጋፎቹን ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደሚደርስ ከንቲባው የገለጹ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘም አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 1 ሺህ 300 የንግድ ቤቶች መታሸጋቸውንም ጠቅሰዋል።