አባይ ሚዲያ መጋቢት 26፤2012

አለም አቀፍ ወረርሺኝ በሆነው የኮቪድ-19 ምክነንያት በቫይረሱ የሚጠቁ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ሆኖ ይቀጥላል ሰሞኑን አስደንጋጭ የሆኑ ቁጥሮችን እያስመዘገበች የምትገኘው አሜሪካ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 1,100 ሰዎችን በቫይረሱ አጥታለች ይህም በአንድ ቀን ውስጥ ከተመዘገበው የሞት ቁጥር ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

የኒው ዮርክ ግዛት በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁት ቀዳሚዋ ስትሆን የሟቾች ቁጥር ወደ 2,935 ከፍ ብሏል እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ በአሜሪካ እስካሁን 278,458 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 7,000 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል በተደጋጋሚ ከፍተኛ ቁጥር እያስመዘገበች የምትገኘው እና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለሳምንታት በእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ያለችው ስፔን በ24 ሰዓታት ውስጥ 809 ሰዎችን በቫይረሱ አጥታለች፡፡

ይህም የሟቾቹን ቁጥር 11 ሺህ 744 አድርሶታል እስካሁን 124 ሺህ 736 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ቁጥር በቫይረሱ ክፉኛ እየተጎዳች ካለችው ጣሊያንም የበለጠ ነው ተብሏል በዩናይትድ ኪንግደም ተጨማሪ 684 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ይህም አጠቃላይ የሟቾቹን ቁጥር 3 ሺህ 605 አድርሶታል። እስካሁን 38 ሺህ 168 ሰዎችም በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በኬኒያ ተጨማሪ አራት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሦስት ኬንያዊያን እና ሌላኛው ፓኪስታናዊ እንደሆነ ተነግሯል ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 126 አድርሶታል በተመሳሳይ አንድ የኬንያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ከውጭ ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ማንኛውም ሰው መፈጸም ያለበትን ወደ ለይቶ ማቆያ የመግባት ግዴታን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ታስረዋል።

የባሕር ዳርቻ የኬንያ ግዛት ኪሊፊ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ጌዲዮን ሳቡሪ በግድ ወደ ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት ከገቡ በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ህክምና ሲከታተሉ ቆይተዋል ምክትል አስተዳዳሪው በአሁኑ ወቅት ከበሽታው ሙሉ በሙሉ በመዳናቸው የኬንያ መንግሥት ያወጣውን ደንብ ተላልፈዋል በሚል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በአገሯ ያለው የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰ የምትገኘው ደቡብ ኮሪያ በዛሬው እለት 94 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ይህም በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 10,156 ከፍ ሲያደርገው እስካሁን ድረስ ደግሞ 177 ሞት ተመዝግበዋል።