በቅርብ ጊዜ ጓደኛቼና እኔ ለስራ ጉዳይ ወደ አንድ የመንግስት መሥሪያ ቤት አቀናን ፡፡ ለሄድንበት ጉዳይየሚመለከታቸው ከተባሉ አላፊዎች ጋር በአንድ ጥሩ የመሰብሰቢያ ክፍል ውስጥ ገባንና ስለመጣንበት አጀንዳጨዋታ ያዝን ፡፡ በመሃል ከርዕስ ወጥተን ይመስለኛል ሥለምርጫው ማውጋት ጀመርን ነገር ግን ማንም ከአጀንዳውወጣን ያለ የለም ፡፡ የምርጫው ነገር የሁላችንንም ትኩረት የሳበ ነውና ….
ታዲያ በጨዋታችን መሃል አንዱ ሰው እነዲሀ አለ፣
‹‹አሁን እኮ! ምርጫ የለም ማዛመድ ነው ያለው›› አለ
….ሁላችን ፈገግ አልን…… ፡፡ ፈገግታው ግን አልቆየም….እንደ ጉም በነነ….፡፡ የሁላችንም ፈገግታ ላይ ትካዜ ካባውንደረበ፡፡ ይህ ሰው ምርጫ የለም ማዛመድ ነው ያለው የሚለውአገላለጹ ደርሶ ከሚያሰፈግገው ዋዛ ባሻገር በውስጡ የያዘው እውነት ግን በርግጥ መራራ ነው፡፡ ምረጫው ለምን አሳሳቢሆነ ከተባለ፣ ዓለም እጅግ የሚፈራውና የዲሞክራሲን እድገትየሚበላ ምስጥ ነው የተባለው የማንነት ድምጽ () የኢትዮጵያንፖለቲካ ስለተጣባው ነው፡፡
ሃገሮች በማህበራቸው ውስጥ ሲስተም ዘርግተው ሲኖሩበየጊዝው የሚመርጧቸውን ምርጫዎች የማንነት ድምፅከተጣባው ያ ሀገራዊ ማህበር ከዲሞክራሲ ጋር ተጋጭቷል፣ የማህበሩን መንጋ የሚያምስ ተግባር ዉስጥ ገብቷል ማለትነዉ፡፡ በማህበራችን ዉስጥ ማንነትን እያሸተትን ደምና አጥንትእየቆጠርን ለምርጫ ከወጣን የምርጫ ድግሳችን ሁሉበዴሞከራሲ ፊት የረከሰ ይሆንብናል፡፡ ምርጫ ለማህበራችንተስፋ የሚሆነው ከማንነት ድምጽ ጸድተን የከወንነው እንደሆነብቻ ነው፡፡ የማዛመድ የምረጫ ሰሌት ውስጥ ገብተን የጋራ ቤትሊያምረን አይችልም፡፡ የማዛመድ የምርጫ ድግስ ደግሰንየዴሞክራሲን ስም እየጠራን ምለን ብንገዘት ዴሞክራሲየዚህን ድግስ ጽዋ አይቀምስም፡፡
በዴሞክራሲ የበለጸጉ ሃገራት ዘወትር ምርጫን ተስፋየሚያደርጉት መድብለ ፓርቲ ስርዓት ስለገነቡ ነው፡፡ ምርጫችንከማዛመድ ወዲያ ማዶ ተሻገሮ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ካልገነባንየረጋ ሃገር አይኖረንም፡፡ ሽግግራችን የሚሰምረው ከማንነትድምጽ ስንወጣ ነው፡፡ የመድብለ ፓርቲ መሰረት የሃሳብ ምርጫነው፡፡ ሃሳብ ገስጋሽ ነዉና ከአንዱ ሃሳብ የሌላዉ ይሻላል እያልንመምረጥ ለማህበረሰባችን እድገት ይበጃል፡፡ አለም ወደሪፐብሊክ ስትገባና የስልጣን ምንጩ ራሱ ህዝቡ ነዉ ስትልምርጫዋን የማዛመድ ስራ ለማድረግ አይደለም፡፡ ሃሳብንበማጋጨት የሚመጣውን ምርጥ ሃሳብ ለሁለንተናዊ እድገትለመጠቀምና በየማህበሩ ውስጥ በመተሳሰብ በጋራ ለማደግነው፡፡
ሃገራችን ኢትዮጵያ የማንነትን ድምጽ በገሃድ ከፍ አድርጋየምትኖር ሃገር ናት፡፡ ይሄ ችግር የማህበረሰብን ግንኙነትናትስስር ሁሉ ያበላሸ ልምድ ነዉ፡፡ ኢትዮጵያ ለነገሩ ይህምአይመጥናትም ነበር፡፡ ከማንነት ድምጽ ወጥተን ሃሳብንመምረጥ ስንችል ነው ማህበረስባቸን ወደ ዲሞክራሲየሚሻገርው፡፡ ትግሬው ትግሬውን…. አማራው አማራውን…… ጉራጌው ጉራጌውን —— እየመረጥን ደግሞ የጋራ ቤት፣ የተሸለ ማህበረሰብ ልናስብ አንችልም ፡፡ ስለዚህ ምርጫችን ከማዛመድ ወጥቶ ወደ መድበለ ፓርቲስርአት መሻገር ያስፈልገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ዋናተፈላጊ ለውጥ ወይም ሽግግር ይሄ ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!