አባይ ሚዲያ መጋቢት 28፤2012

በኬላዎች ላይ ጥብቅ የቁጥጥር ሥራ እየተሰራ ነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በአገሪቱ መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ አስታውቀዋል፡፡

የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በሃያ ዘጠኝ የአገሪቱ መግቢያና መውጫ ኬላዎች እንዲሁም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በኢትዮጅቡቲ የመግቢያ ኬላ ላይ በሽታው ወደ አገር ውስጥ ገብቶ እንዳይስፋፋ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ በ14 ቅርንጫፎች ሰው በሚገባባቸውና በማይገባባቸው 94 ኬላዎች ላይ ክትትል እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በቀጣይ ወረርሽኙን ለመከላከል በየዕለቱ መረጃ ለመለዋወጥና ከክልልና ከፌዴራል የጤና ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጀይላን ኡመር ተናግረዋል፡፡