አባይ ሚዲያ መጋቢት 30፤2012

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ ሶስት ግለሰቦች የኮቪድ-19 ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ ዛሬ መጋቢት 30/2012 ዓ.ም ቀን አጋማሽ አካባቢ ያሉትን መረጃዎች ስንመለከት  ድግሞ በዓለማችን 1 ሚሊዮን 432 ሺህ 686 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 302 ሺህ 324 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 82 ሺህ 124 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል ያገገሙት ሕይወታቸውን ካጡት ጋር ሲነጻጸር በ220 ሺህ 200 ይበልጣሉ ይህም ያገገሙት ሕይወታቸውን ካጡት በአራት እጥፍ አካባቢ እንደሚበልጥ ያሳያል፡፡

በአሜሪካ ብቻ 400 ሺህ 540 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 21 ሺህ 711 አገግመዋል፤ 12 ሺህ 857 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል አሜሪካ በዓለማችን በቫይረሱ የተያዙ ብዙ ሰዎች ያሉባት ቀዳሚዋ ሀገር ናት ሞት በማስመዝገብ ግን ጣሊያን ናት ቀዳሚዋ፡፡

በጣሊያን 135 ሺህ 586 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 24 ሺህ 392 ሲያገግሙ 17 ሺህ 127 ሰዎች ግን ሕይወታቸውን አጥተዋል እጅን በሳሙናና በውኃ በሚገባ መታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ከሚስሉና ከሚያነጥሱ ሰዎች ሁለትና በላይ ሜትር መራቅ ወረርሽኙን ለመግታት እንደሚያስችሉ በጤና ባለሙያዎች ይመከራል፡፡

ከዚህ ባለፈ አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ ከቤት አለመውጣት እና በመንግሥት የተላለፉ መመሪያዎችን መተግበርም ራስን፣ ቤተሰብንና ኅብረተሰቡን ከወረርሽኙ ለመጠበቅ እንደሚያግዙ ይታመናል ይህንን በማድረግ ራስን ለጥንቃቄ እንጂ ለጭንቀት አለማጋለለጥ ተገቢ እንደሆነም ነው በሥነ ልቦና ባለሙያዎች የሚመከረው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቫይረሱ መቀስቀስ ምክንያት ቀድማ የተቆለፈችው የቻይና ከተማ ቀድማ ተከፍታለች የውሃን ከተማ ነዋሪዎችም “የዓለም ሕዝብ ከእኛ ስህተት ሊማር እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።