አባይ ሚዲያ መጋቢት 30፤2012

በአማራ ክልል ላሊበላና አካባቢዎች በፋኖ አደረጃጀት ውዝግብ በተፈጠረ ሁከት የሰው ህይወት ማለፉን የአይን እማኞች ለአባይ ሚዲያ ተናግረዋል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የላሊበላ አካባቢ የፋኖ አባል ለአባይ ሚዲያ እንደተናገሩት በላስታ ላሊበላ ወረዳ ብልባላ የተሰኘች የገጠር ቀበሌ አካባቢ የክልሉ መንግስት ታጣቂዎች በተለይም የልዩ ሀይል አባላት በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸውልናል፡፡

በተቀሰቀሰው ሁከትም ማዕረጉ ተማረ እና ሲሳይ ደባልቄ የተባሉ የፋኖ አባላትና በአካባቢው የነበረች አንዲት ሴት ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል በጉዳዩ ላይ ከመንግስት በኩል ያለውን መረጃ ለማግኘት ለላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ብርሀኑ ደውለን የነበረ ቢሆንም አስተዳዳሪው ጥያቄያችንን ካደመጡ በኋላ መረጃውን አሰባስቤ እነግራችኋለሁ በማለት አሁን ላይ ምንም ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡