አባይ ሚዲያ ሚያዚያ 01፤2012

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ “የግድያ ዛቻ ደርሶብኛል፤ እኔ ግን ግድ አይሰጠኝም” ሲሉ የተቃጣባቸውን ጥቃት ጠንከር ባሉ ቃላቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ አጣጥለዋል “ከሁለትና ከሦስት ወር በላይ ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ጥቁር፣ ባርያ ተብያለሁ፤ እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ፤ የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም” ሲሉም አክለዋል።

“በዘረኛ ንግግር በግል ጥቃት ሲደርስብኝ የበታችነት ስሜት ስለማይሰማኝ ምንም አይመስለኝም። ምክንያቱም እኔ ኩሩ ጥቁር ነኝ” ኃላፊው በሰጡት መግለጫ ላለፉት ሦስት ወራት እሳቸው ላይ ያነጣጠሩ ዘለፋዎች እንደተሰሙ ገልጸው ሆኖም ግን እሳቸውን የሚያሳዝናቸው አህጉሪቱ ላይ የተቃጡ ጥቃቶች መሆናቸው እንደሆኑ አክለዋል።

“መላው ጥቁር ሕዝብ እና መላው አፍሪካ ሲዘለፍ ግን አልታገስም፤ ያኔ ሰዎች መስመር እያለፉ ነው እላለሁ ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ እኔ የግድያ ዛቻ ሲደርስብኝ ምንም አልመሰለኝም፤ መልስም አልሰጠሁም እንደ ማኅበረብ ሲሰድቡን ግን መታገስ የለብንም” ብለዋል።