አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 07፤2012

አሜሪካ ለዓለም የጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ በማቋረጧ የምትጎዳው ራሷ እንደሆነች አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮቪድ 19 መስፋፋትና እያደረሰ ላለው ጉዳት የዓለም ጤና ድርጅትን መውቀሳቸው የሚታወቅ ነው ፕሬዝዳንቱ በተለይም በአሜሪካ የተጠቂ ሰዎችና የሟቾች ቁጥር በማሻቀቡ “ለደረሰው ጥፋት ድርጅቱ ተጠያቂ መሆን አለበት” እስከ ማለት ደርሰዋል ትራምፕ ለበሽታው መስፋፋትም ምክንያቱ የአለም ጤና ድርጅት እንዝህላልነት ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚያም ሲያልፍ ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ለድርጅቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ዋነኛ ድጋፍ አድራጊ ሆኖ ሳለ ለቻይና ወግኗል ያሉ ሲሆን ከአሜሪካ በወረርሽኙ መጠቃት ጋር ተያይዞም በቅደመ መከላከል ዙሪያ ድርጅቱ የሰራው ስራ እጅግ ዝቅተኛ ነው ሲሉም ደጋግመው ተናግረዋል በዚህ ያላበቁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለዓለም ጤና ድርጅት የምታበረክተውን የገንዘብ መዋጮም እንዲቋረጥ አዘዋል ይህም ማለት አሜሪካ ለድርጅቱ በየዓመቱ ለድርጅቱ ትሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቆም የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግስት የበሽታውን ስርጭትና የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ያደረገው ጥረት ማነስና በሽታው በሀገረ ቻይና እንደተከሰተ የቻይና ጉንፋን ነው እኛን አያሰጋንም ያለው ቀርቶ በሳምንታት ልዩነት አሜሪካ ቀዳሚዋ የኮቪድ 19 ተጠቂና ሟች ያስተናገደች ሀገር ሆናለች የትራምፕ የመጣውን አደጋ ያላገናዘበ ንግግርና በተጓደለ ጥንቃቄ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለቫይረሱ ሲጋለጡ ጥቂት የማይባሉም ህይወታቸው አልፏል በአገራቸው ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ለቫይረሱ ባሳዩት ቸልተኝነት ክፉኛ እየተብጠለጠሉ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ በአንዳንድ የሀገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች በዓለም ጤና ድርጅት ላይ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ የተወሰነ ፋታ ለማግኘትና ትኩረት ለማስቀየር እንደሆነ እየተገመተ ይገኛል፡፡

ትራምፕ በሀገራቸው የተደቀነውን አደጋ በሌላ አካል ለማላከክና ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማሸሽ ሲሉ ነው በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራውን የዓለም ጤና ድርጅት እየከሰሱ ያሉት የሚሉ ወገኖችም አሉ ይህንኑ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ አባይ ሚዲያ ያነጋገራቸው የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ውሳኔው አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የመሪነት ሚናና ተፀዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳጣ በመሆኑ በዚህ የምትጎዳው ራሷ ናት ሲሉ የግላቸውን አስተያየት ሰንዝረዋል አቶ ጌታቸው አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት አሜሪካ የምታደርግለትን ድጋፍ ብታቋርጥም ድርጅቱ ስራውን መቀጠሉ አይቀርም ነገር ግን ሀገሪቷ ያላትን አለም አቀፍ ተደማጭነትና ተሰሚነት ያሳጣታል ብለዋል፡፡