አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 13፤2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ተገን ጥያቄዎች ሂደት ላይ ያደረገዉ ለዉጥ የኤርትራ ተገን ጠያቄዎችን እና ሕጻናትን ተገቢ ከለላ የሚያሳጣ ነዉ ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዉ ድርጅት ሂዉማን ራይትስዎች አስታውቋል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ኤርትራዉያን ስደተኞች ያላቸዉን ለጥገኝነት የማመልከት መብት እና በመጠለያ ጣብያ አስተዳደር ላይ የሚያደረጉትን ለዉጥ ለሁሉም ለስደተኞች በይፋ የማሳወቅ አለባቸዉ፤ ይላል ድርጅቱ መግለጫዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ባለፈዉ ጥር ወር ለዓመታት ሲሰራበት የቆየዉን እና ሁሉን ኤርትራዉያን ስደተኞች በብድን ተገን የማገኙበትን የስደተኝነት ፖሊሲ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ቀይሮአል ሲል ድርጅቱ ወቅሶአል።

የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሻች ጉዳይ አስተዳደር በኤርትራ ድንበር በኩል ከገቡት በርካታ ኤርትራዉያን ስደተኞች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ በስደተኝነት መመዝገባቸዉን ይሁንና ብቻቸዉን የተሰደዱ ሕጻናት እና ሌሎችም በስደተኝነት አለመመዝገባቸዉን የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች የርዳታ ድርጅቶች ገልፀዋል ይህ ድርጊት ስደተኞቹን ወደ ጥቃትና ጭቆና ወደአለበት እንዲመለሱ በማድረግ የዓለምአቀፉን የስደተኞች ሕግ ይጣረሳል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ተችቶአል።

የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪቃ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲቲያ ባደር ለረጅም ዓመታት ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ስትቀበል መኖርዋን በመግለጫዉ ላይ ተመልክቶአል። አሁን ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ለኤርትራውያኖች በተለይም ወላጅ፤ አሳዳጊ ለሌላቸዉ አልያም ብቻቸዉን ለሆኑት ሕፃናት ኤርትራዉያን ስደተኞች ጥበቃ መከልከል የለበትም” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ባለፈዉ ታህሳስ ባወጣዉ መረጃ መሰረት በትግራይ መጠለያ ጣብያ ከሚገኙ ኤርትራዉያን ስደተኞች መካከል 44 በመቶ የሚሆኑት ልጆች ናቸዉ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤርትራ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል ጥረት ላይ ነኝ ብላለች ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ የኮቪድ-19 ወርርሺኝን «ያጋጥማል ተብሎ ያልተገመተ ድንገተኛ ጦርነት» ሲሉ ገልፀዉታል።

በዚህም የቫይረሱ መነሻና ቀጣይ የስርጭት ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ስለሆነ አሁን ላይ ብቸኛው መፍትሔ ወረርሺኙ እስቀሚያበቃ ድረስ “ባለህበት መቆየት” ነው ሲሉ ፕሬዝደንቱ ለሀገራቸው ህዝብ በቴሌቭዥን ባሰራጩት መልእክት አስተላልፈዋል  የሀገሪቱ መንግስት በሽታውን  ከመከላከል በተጨማሪ የልማት ተግባራቱን ጎን ለጎን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝደንት ኢሳያስ በንግግራቸው ቃል ገብተዋል፡፡

እንደ ኤርትራ ጤና ሚኒስቴር መረጃ በሀገሪቱ እስካሁን በቫይረሱ የተለከፉ ሰዎች ቁጥር 39 የደረሱ ሲሆን ሰዎች ከህመማቸው አገግመዋል ኤርትራ ቫይረሱን ለመከላከል ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን በረራዎችና በሀገር ውስጥም ከቦታ ወደ ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴ ያገደች ሲሆን ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋማትም ዘግታለች፡፡