አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 21፤2012

በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን መደበኛ ባልሆነ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦችን መፈናቀል ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳስበዋል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት “መደበኛ ባልሆነ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማፈናቀል በጊዜያዊነት ሊታቀብ ይገባል” ብለዋል።

በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን መደበኛ ባልሆነ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከመኖሪያችን አታፈናቅሉን ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በልማት ምክንያት ቤታቸው ለፈረሰባቸው ዜጎች ምትክ መኖሪያ ሰጥቻለሁ፣ገሚሶቹ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የሰፈሩ ናቸው የሚል ሀሳብ ያነሳል።

ይሁንና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ደግሞ ድርጊቱን ለጊዜው መቆም ይኖርበታል የሚል የመፍትሔ ሃሳቦችን ሰንዝሯል ‹‹መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና የቤት ግንባታ መስፋፋት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞች ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው ሆኖም በአሁኑ ኮቪድ19 ወቅት ቤተሰቦችን በሃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ በተለይ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ትልቅ አደጋ አለው፡፡

አዳዲስ መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና መደበኛ ያልሆነ የቤት ግንባታን መከላከል ያስፈልጋል። ነገር ግን በዚህ የአስቸካይ ጊዜ ወቅት መደበኛም ባይሆኑም ነባር ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማስወጣት ለጊዜው እንዲታቀብ”ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል ይህ በእንዲህ እንዳለ ስራ አልባ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ተገደው እየወጡ ቤት አልባም እየሆኑ ነው ሲል አመንስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ወቅሷል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል አቅሙ የሌላቸውን፣ መተዳደሪያቸው የቀን ስራ የሆነ የከተማዋ ነዋሪዎችን መንግስት አስገድዶ እያፈናቀለ ነው ሲል የአለም አቀፉ የመብት ተሟጋች አምነስቲ በድረ ገፁ ባወጣው ሪፖርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወቅሷል እንደ አምነስቲ ፤ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ 1 ሺህ ሰዎች ቤት አልባ የሆኑ ሲሆን እነዚህ ሰዎችም ባመዛኙ ሃገሪቷ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ባስተላለፈችው የእንቅስቃሴ ገደብ የጉልበት ስራቸውን ያጡ ናቸው ብሏል፡፡

የጸጥታ ሀይሎች ለጊዜው ዝናቡን ቢያስጠልለን ብርዱን ቢቀንስልን ብለው ያዘጋጁትን የሸራና የፕላስቲክ መጠለያ እያፈረሱ እንደሚያበርሯቸው ጨምሮ ገልጧል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቼና እንደተናገሩት የተፈናቀሉት ቤተሰቦች እንዴት ልጆቻቸው በዝናብና በብርድ ደጅ እያደሩ እንደሆነ አሰቃቂ ታረክ ነግረውናል ብለዋል፡፡

አለም በበሽታው ጭንቅ ውስጥ በአለበት በዚህ አስከፊ ወቅት ቤት እያፈረሱ ቤት አልባ ማድረግ ሰብአዊነት የጎደለው አሳዛኝ ተግባር ነው ያለው መግለጫው ባለስልጣቱ በአስቸኳይ ይሄንን ማፈናቀል ማቆም እንዳለባቸውና አማራጭ ቤት ማቅረብ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሷል አምነስቲ ከሳተላይት አገኘሁት ባለው ምስል ከቦሌ አለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በቅርብ የተገነቡ 40 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡