አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 22፤2012

በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት በነሐሴ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ ማስፈጸም አስቸጋሪ በመሆኑ መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም ምርጫውን ማካሄድ ያስችላሉ ያላቸውን አራት አማራጮችን ማቅረቡ ተነግሯል እነዚህም አማራጮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ህገ መንግስት ማሻሻል እና የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው።

ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እነዚህን አማራጮች ካቀረቡ በኋላ አንዳንድ ፖለቲከኞች ‘አራቱም አማራጮች ጥሩ አይደሉም ሲሉ ተደምጠዋል’ በተለይም መንግስት የህገ መንግስት አማራጭ አቀርባለሁ እያለ የሚጣደፈው ስልጣኑን ማራዘም ስለሚፈልግ ብቻ ነው ሲሉ መከራከሪያ ያቀርባሉ ገለልተኛ የሆኑ የህግ ባለሙያዎች የቀረቡ አማራጮች ያሏቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች አብጠርጥረው ያስቀምጣሉ፡፡

የዲሞክራሲ እና የአስተዳደር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አደም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን ማለት በቀላል ቋንቋ የምክር ቤቱ አባላት የሥራ ጊዜ እንዲያበቃ ማድረግ እና መንግሥት ግን የዕለት ተዕለት ሥራውን እያከናወነ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሆነ ይናገራሉ “የምክር ቤቱ አባላት ይበተኑ እንጂ የመንግሥት ካቢኔ ግን ይቀጥላል” ይላሉ።

ዶ/ር አደም መንግሥት ምርጫ ለማስፈጸም አማራጭ ይሆናሉ ብሎ ካቀረባቸው አመራጮች መካከል ይህ የተሻለው አማራጭ ይሆናል ብዬ አላስብም ብለዋል ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚንስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ከበተኑ በኋላ የሚኖራቸው መንግሥት ‘ደካማ’ የሚባል ይሆናል።

ሁለተኛ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ደግሞ ፤ “ይህ እንደ አማራጭ ሆኖ መታየቱ የግንዛቤ ችግር እንዳለ ያሳያል። ምክንያቱም ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 60 የፓርላማው እና የመንግሥትን እድሜ ከአምስት ዓመት ለማሳጠር እና ምርጫ ለማካሄድ ታስቦ የተቀመጠ እንጂ የመንግሥትን እድሜ ለማራዘም ታስቦ የተቀመጠ አይደለም” ይላሉ የሕግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሔኖክ ገቢሳ በበኩላቸው በአንቀጽ 60 መሠረት ምክር ቤቱ የሚበተነው የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት አዲስ ምርጫ ለማካሔድ እንጂ መንግሥት የራሱን ስልጣን ለማራዘም በማሰብ አይደለም ይላሉ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መበተኑ አዋጭ አካሄድ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ገቢሳ “ምክር ቤቱ ተበተነ ማለት መንግሥት ተበተነ እንደ ማለት ነው። ከመንግሥት ከሶስቱ የመንግሥት መዋቅሮች  ትልቅ ስልጣን ያለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ትልቁን የመንግሥት አካል ተበተነ ማለት ሕጎች ማውጣት አይችልም፣ ሚንስትሮችን እና የካቢኔ አባላትን ማስሾም አይችልም” ይላሉ በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ሥልጣን እንዳለው ዶ/ር አደም ያስታውሳሉ።