አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 24፤2012

ምርጫ በመራዘሙ ምክናየት ይመለከተናል የሚሉ አካላት ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ እነ አቶ ጀዋርም ችግሩን ለመፍታት ብቸኛውና የተሻለው አማራጭ ለችግሩ ፓለቲካዊ መፍትሄ መሻት እንደሆነ ሲገልጹ ቆይተዋል ፖለቲከኛው ሕገመንግሥታዊ ቀውሱን በንግግር እና ድርድር ፖሊቲካዊ መፍትሄ መሻት ነው የሚሻለው ሲባል አንዳንዶች በሽምግልና፣ በልምምጥ ብሎም ህገመንግስቱን ንደን እንሂድ የተባለ ይመስላቸዋል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

አቶ ጀዋር ይህ ፖለቲካዊ ስምምነት የሚዘጋጅበትን ሂደት ሲያብራሩ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ሀይሎች እና ማህበራዊ ቡድኖች የሚወከሉ፣ አንዳንዴም በቀጥታ በሕዝብ በሚመረጡ ተወካዮች፣ በባለሙያዎች እገዛ አማካኝነት፣ በሰነዱ መካተት ያለባቸው የስምምነት ነጥቦች ላይ ውይይት፣ ክርክር እና ድርድር ይካሄዳል ይላሉ።

በተወካዮቹ ስምምነት ላይ የተደረሰበት ረቂቅ ሰነድም ለሕዝበ-ውስኔ ቀርቦ ከፀደቀ የሀገሪቷ የበላይ ሕግ ሆኖ እንደሚያገለግል ያብራራሉ በአቶ ጀዋር እይታ ገዢው ፓርቲ ያቀረባቸው መፍትሄዎች የማያስኬዱ ናቸው ምክናየቱ ደግሞ በገዢው ፓርቲ እንደ ተመራጭ መፍትሄ እየተቀነቀነ ያለው የሕግ መተርጎም አካሄድ ቀድሞውኑ ጉዳዩ ስምምነት ያልተደረሰበትና በህገ መንግስቱም ያልተካተተ በመሆኑ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ህገ መንግስትን የማሻሻልም ሆነ የመተርጎም ሥልጣን የተሰጣቸው የፌደራል እና የክልል ምክር ቤቶች ቢሆኑም አሁን ያሉት የምክር ቤት አባላት በተጭበረበረ ምርጫ ሥልጣን የያዙ እና የአንድ ፓርቲ አባላት በመሆናቸው እንደሆነ አቶ ጀዋር ያብራራሉ ምክናየቱም በተጭበርበረ ምርጫ ሥልጣን የያዙ የአንድ ፓርቲ አባላት የሚያስቀምጡት መፍትሄ ሀገራዊ ስምምነት ሳይሆን በአንድ ወገን የሚጫን አድሎአዊ ውሳኔ እንደሚሆን ግልፅ ስለሆነ ምርጫው ባለመካሄዱ የሚፈጠረውን የመንግሥት ቅቡልነት ችግር ያባብሳል እንጂ አይፈታውም ብለዋል::

ስለዚህ ለዚህ ቀድሞ ስምምነት ላይ ላልተደረሰበት ጉዳይ እና እንደ አዲስ ለተጋረጠብን ችግር መፍትሄው አዲስ ስምምነት ላይ መድረስ ነው የሚሉት የኦፌኮ አባሉ አቶ ጀዋር የምርጫ ጉዳይ በዋነኛነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ ስልሆነ፣ በምርጫ ቦርድ ሕጋዊ መስፈርት ያሟሉ ፓርቲዎች የሚደርሱበት ጊዜያዊ ስምምነት ምርጫውን ማስተላለፍ እና ምርጫው እስኪካሄድ መንግሥት የሚመራበትን ማዕቀፍ ማበጀት እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረገውን ሂደትም ማስተባበር ያለበት አካል እስካሁን እንደነበሩት  በምርጫው ከሚፎካከሩ ፓርቲዎች የአንዱ መሪ በመሆኑት ጠ/ሚ ዐቢይ መሆን አይችሉም ያሉት አቶ ጀዋር አደራዳሪው ከተደራዳሪዎቹ አንዱ ሊሆን እንደማይችል በምክናየትነት ያነሳሉ።

ለዚህ ሚና የሚመጥነው አካል ሁሉም ፓርቲዎች ተስማምተውበት የሚመርጡት አደራዳሪ መሆን እንዳለበት ፖለቲከኛው ጠቅሰዋል።

ያ ካልተቻለ ደግሞ ድርድሩን ሊያካሂዱ የሚችሉት አሁን ካሉት የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በምርጫ ውጤት ላይ ቀጥተኛ ባለድርሻ ያልሆነ አካል መሆን እንደሚኖርበት አቶ ጀዋር ጠቁመዋል::