አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 27፤2012

ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከአለም አቀፉ የሰው ህይወት ህልፈት አንጻር ሲታይ ይህ ነው የሚባል የከፋ ሞት አለማስመዝገቧ ብዙዎችን አዘናግቷል  ሲሉ  የህክምና ባለሞያዎች  ሲናገሩ ሰንብተዋል በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1047 ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተካሂዶ 5 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3ቱ ሴቶችና  የተቀሩት ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተናግሯል።

ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ካሳወቀው የናሙና ውጤት  መካከል አንድ ሞት መመዝገቡንም አሳውቋል በቫይረሱ የሞቱት የ75 ዓመት ሴት አዛውንት ሲሆኑ በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ እና ባጋጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮቪድ-19 ተጠርጥረው ለምርመራ ናሙናቸው ቢወሰድም ውጤታቸው ከመታወቁ በፊት ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

እኚህ አዛውንት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ኖሯቸው እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሆነ በመግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ይሄም ያለ ጉዞ ታሪክ የተጠቂዎች ቁጥር በሂደት እንዲበራከት አድርጓል በጤና ሚንስቴር እና በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ መሠረት በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ከጂቡቲ ተመልሰው በአፋር ክልል በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የነበሩ ሁለት የ25 ዓመት ወንዶች ይገኙበታል።

የተቀሩት ደግሞ የ8 እና የ19 ዓመት ሴቶች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው መሆኑ ተነግሯል የወረርሺኙ አለም አቀፍ ስርጭት ሲታይ ደግሞ አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ዝቅተኛውን የሞት መጠን እንዳስመዘገበች አስታውቃለች።

የሟቾችም ቁጥር 1015 ሲሆን ይህም ከአንድ ወር በኋላ ዝቅተኛው መሆኑ ተጠቁሟል በአሜሪካ እስካሁን ከ 1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህ ቁጥር በስፔን ከተመዘገበው በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን ከቻይና ደግሞ በ 14 እጥፍ ይበልጣል እስካሁን ደግሞ 200 ሺ የሚሆኑት ከቫይረሱ አገግመዋል።

የአሜሪካ መንግስት በሰራው ጥናት መሰረት በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከዚህም በላይ በፍጥነት የሚጨምር ሲሆን የሟቾች ቁጥር ግን በመጪው ሰኔ መቀነስ እንደሚያሳይ  ተዘግቧል የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው አሁናዊ መረጃ መሰረት በመላው ዓለም ኮሮናቫይረስ ለሕይወታቸው ማለፍ ምክንያት የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከእሩብ ሚሊዮን አልፏል።

እስካሁን ከፍተኛ ዜጋ የሞተባት አሜሪካ ስትሆን 69 ሺ ሰዎችን በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች ጣልያን ለ30 ሺ የቀረበ ሰው እንደሞተባት ያስታወቀች ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ወደ 29 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ምንም እንኳን በእነዚህ አገራት የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም የዓለም ጤና ድርጅት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማላላት ተገቢ አይደለም ሲል  አሳስቧል፡፡