አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 27፤2012

የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 23-25 በክልሉ እና በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው አስታውቋልnመንግሥት ምርጫውን በቀጣይ ለማካሄድ ካስቀመጣቸው አመራጮች አንዱ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚለው አንዱ ነው ህወሐት በመግለጫው “የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-መንግስቱን ለመተርጐም በሚል ሰበብ የጀመረውን ገሀድ የወጣ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆም” ሲል ጠይቋል።

ህወሐት የትግራይ ህዝብ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዳለው በማስታወስ፤ ለትግራይ ህዝብ ሙሉ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል ብሏል ህወሓት መንግሥት የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ማለቱን ተከትሎ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚደቅሳ “የክልሉ መንግሥትም ሆነ ክልሉን ሚያስተዳድረው ፓርቲ ምርጫ ማካሄድ ሕጋዊ አይሆንም” ሲሉ  ተናግረዋል።

ህወሐት ምርጫውን በክልል ደረጃ ለማካሄድ ስለመወሰኑ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አለማሳወቁን ወ/ት ብርቱኳን “ለኛ ፎርማሊ የደረሰን ነገር” የለም በማለት አስረድተዋል “ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይሆንም። ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም” ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው ምርጫ ቦርድ እርሳቸው የሚመሩት ብቸኛው ምርጫ ቦርድ መሆኑን በማስታወስ፤ “በፌደራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው ለምርጫ ቦርድ ነው” ብለዋል የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ።

ከዚህ ውጪ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌደራል አስፈጻሚ አካል ተስቶ ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፍ ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንምም ብለዋል ወ/ት ብርቱኳን ከአጠቃላይ ምርጫ በተለየ ጊዜ የአንድ አካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ግን ጠቁመዋል እንደ ምሳሌም፤ ከዚህ ቀደም በሶማሌ ክልል አብዛኛው ድምጽ ሰጪ በኑሮ ዘያቸው ምክያት በድምጽ መስጫ አካባቢ የማይገኙበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበረ በማስታወስ ከአጠቃላይ ምርጫ በኋላ በክልሉ ምርጫ እንደተከናወነ አስታውሰዋል።

በእርግጥ የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል የሚለው አሁን አካራካሪ ሆኖ ቀጥሏል የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው ምርጫን የማካሄድ፣ የምርጫ ሕግን የማውጣት፣ የወጣውን ደግሞ ማስተዳደር ሥልጣን ያለው የፌደራሉ መንግሥቱና ምርጫ ቦርድ ነው ሲሉ ይናገራሉ ከዚያ ውጪ የህወሐት አመራሮች ሕጉን ተከትለው ካልተቃወሙ በስተቀር በራሳቸው ዝም ብሎ መሄድ ስልጣኑም የላቸውም ይላሉ “መንግሥት የሕዝቦች ፈቃድ ነው ስለሚባል ዜጎችን በመምረጥና በመመረጥ ማሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ነፃና ገለልተኛ መሆን አለበት” የሚሉም የህግ ባለሙያዎች አልጠፉም፡፡