አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 28፤2012

ኢዜማ ከኮሮና ወረርሺኝ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የነበሩ የውስጥ ፖለቲካዊ ችግሮች እና በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባን ካለነው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያየዘ ከሌሎች ሀገሮች የተደቀነብን አደጋ በፍፁም በቀላሉ የሚታይ አይደለም ያለው ኢዜማ በተለይም ከግድቡ የውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ተጽዕኖ እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃል ሲል በመግለጫው አብራርቷል፡፡

ምርጫ መራዘምን በተመለከተ  የተለያዩ አካላት ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ነው የሚሉትን ሀሳብ እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቅሶ ኢዜማ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሕግ ባለሙያዎች ባደረገው ሰፊና ጥልቅ ውይይት የመፍትሔ ሀሳቦችን ጠቅሟል ኢዜማ ሀገራዊ ፈተናዎች ለማለፍ ሕዝብን አስተባብሮ ሊመራ የሚችል ጠንካራ መንግሥት እንደሚያስፈልገን አምናለሁ ያለ ሲሆን ነገር ግን  በፖለቲካ ፓርቲዎች ንግግር ላይ የተመሰረተ የሽግግር መንግሥት ሀገሪቱን ሊመራ ይገባል የሚለው አሁን ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች የእርስ በርስ ግንኙነት እና የቁጥር ብዛት ከግምት ያላስገባ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ አይቻልም ብሏል፡፡

የቀረቡ የህግ አማራጮችን  በተመለከተ ኢዜማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፤  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እና ምርጫውን ማራዘምም ሆነ የሕገ መንግሥት ትርጉም ከፌደሬሽን ምክር ቤት መጠየቅ አሁን ላለው ችግር መፍትሄ አይሆኑም ብሏል ነገር ግን በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 104 እና 105/2 መሠረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግ የሚለው አማራጭ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ የማስፈጸሚያ ሥነ ሥርዓት ያለው እና አሁን ለገባንበት አጣብቂኝ የማያዳግም ምላሽ የሚሰጥ ነው ሲል ኢዜማ ይገልጻል፡፡

ምንም እንኳን ኢዜማ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ሊሻሻሉ የሚገባቸው በርካታ አንቀጾች እንዳሉ በፅኑ ቢያምንም አሁን ያለንበት ወቅት ሁሉን አቀፍ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል እንዳልሆነም ያስረዳል ኢዜማ አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱን የሥራ ዘመን የሚደነግገው አንቀጽ 58ን በማሻሻል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ1 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ስልጣኑ እንዲራዘምና እንዳይበተን ሲል አማራጭ አቅርቧል ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከአባይ ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡