አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 29፤2012

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰበብ ከግብፅ ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብ እልባት ባያገኝም ግድቡን በመጪዉ ክረምት መሙላት እንደምትጀምር የዉሐ ሚንስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም ኢትዮጵያ ግድቡን የምትሞላበትን ጊዜ እንድታራዝም ግብፅና ሁለቱን ወገኖች እናደራድራለን የሚሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ግፊት እያደረጉ መሆናቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።

የኢትዮጵያ የዉኃ፣መስኖና ኃይል ማመንጪያ ሚንስትር ስለሺ በቀለ እንዳሉት ግን ግድቡ ከመጪዉ ኃምሌ ጀምሮ ዉኃ እንደሚሞላ የገለጹ ሲሆን ዘንድሮ የሚሞላዉ ወኃ ድግሞ ሁለት ተርባይኖች ማንቀሳቀስ እንደሚችል ተጠቁሟል ግብጽ ደግሞ የውሃ ሙሌቱ አሳስቧት “ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ደቅናለች” ስትል  ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አስገብታለች።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተመለከትኩት ያለው ይህ የግብጽ የአቤቱታ ሰነድ የግብጽ አቤቱታ የአለማቀፉ ማህበረሰብ የድርጊቱን አሳሳቢነት ለኢትዮጵያ እንዲያስረዳ እና ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ ለብቻዋ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳትወስን ይጠይቃል ሰነዱ በህዳሴው ግድብ ላይ የሚከናወን የውሃ ሙሌት የታችኛው ተፋሰስ አገራት ሳይመክሩበት በኢትዮጵያ በኩል እንዳይጀመርም የሚያሳስብ ሲሆን ግድቡ ሲገነባ ጀምሮ ኢትዮጵያ “የታችኛውን ተፋሰስ አገራት ሳታማክር ወደ ስራ መግባቷ የዓለማቀፍ ሕግን የጣሰ ድርጊት ነበር” ስትል ግብጽ በአቤቱታ ደብዳቤዋ ወንጅላለች።

ጉዳዩን የሚከታተሉ ምሁራን ደግሞ በአንድ በኩል የግብጽ ማባበያ በዋነኝነት ትኩረት የሚያደርገው ሱዳን ላይ ነው ይላሉ የሱዳንና ኢትዮጵያ  ወቅታዊ መነጋገሪያ ጉዳይ ደግሞ  የድንበር ውዝግብ ሲሆን የግድቡን ድርድርና የድንበሩ ውዝግብ እንዴት ታርቆ ይሄዳል የሚለው መነጋገሪያ ነው በግድቡ ድርድርና በሱዳን ተጽዕኖ ዙሪያ ከአባይ ሚዲያ ጋር የስልክ ቆይታ ያድረጉት የህግ ምሁሩ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በበኩላቸው የሱዳን አቋም ከሚዲያ ሽፋንና አሉባልታ በዘለለ ለኢትዮጵያ የሚጠቅምን ድጋፍ ስትሰጥ አይስተዋልም ያሉ ሲሆን በተጨማጭ ሱዳን የቀየረችው አቋምና ከኢትዮጵያ ጎን ለመሰለፏ የታዬ ነገር እንደሌለ ነግረውናል፡፡