አባይ ሚዲያ ሚያዝያ 29፤2012

የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ ኢ-ሕገ መንግስታዊ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ “በሀገሪቱ ምርጫ ማድረግ የሚችለው በሕገ መንግስቱ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድ የምርጫ ቦርድ ብቻ በመሆኑ ምርጫ ይደረጋል ብሎ መግለጫ ማውጣት ከሕገ መንግስት ውጭ መሆን ነው” ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ማናቸውንም ዓይነት ምርጫዎች የማካሄድና የማስተባበር ሥልጣን ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑን ያነሱት አቶ ነብዩ ከዚህ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት ያፈነገጠ አካሄድ ካለ እርምት እንደሚያስፈልገውና ወንጀል ተብሎ ሊጠቀስ እንደሚችልም አስታውቀዋል ህወሓት ከዚህ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት እንዲቆጠብ ብልጽግና በተለያየ መንገድ እያሳሰበ እንደሆነም ተናግረዋል ከዚህ ድርጊት የማይታረሙ ከሆነ ግን ሕጉን የተከተለ እርምጃ ለመውሰድ መንግስትና ብልጽግና ፓርቲ አቋም ስለመያዛቸውም ነው የተናገሩት፡፡