አባይ ሚዲያ ግንቦት 08፤2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን አላሟሉም ያላቸውን 27 ፓርቲዎች መሰረዙን ሲያስታውቅ ፓርቲዎቹ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና ምዝገባ ጀምረው የነበሩ ናቸው በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ እንዲያቀርቡ ለ106 ፓርቲዎች ደብዳቤ ጽፌ ነበር ያለው ቦርዱ 76ቱ ብቻ ሰነዶችን ማቅረባቸውን ገልጿል፡፡

በፖለቲካ ፓርቲዎቹ የቀረበው ሰነድ በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ እንደሚገኝም ነው ያስታወቀው ስራው እንደተጠናቀቀም ከ76ቱ መካከል ምን ያህሉ መስፈርቱን እንዳሟሉ በቦርዱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ነገር ግን የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ማስገባት ያልቻሉ እና ጊዜ እንዲራዘምላቸው የጠየቁ 15 የፓለቲካ ፓርቲዎች ሲኖሩ ከነዚህ ፓርቲዎች መካከል የ13ቱ አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰረዙ ቦርዱ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል ከቦርዱ በተደረገው ጥሪ መሰረት ሰነዶቻቸውን ያላቀረቡ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሃዳቸውን የገለጹ ሌሎች 14 ፓርቲዎችም ተሰርዘዋል የመስራች አባላት ዝርዝር ባለማቅረባቸው ምክናየት በምርጫ ቦርድ ከተሰረዙ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ኢሃን የሚገኝበት ሲሆን ፓርቲው ውሳኔውን አጣጥሎታል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በጉዳዩ ዙሪያ ከአባይ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ውሳኔው ህገወጥ ነው ያሉ ሲሆን የምርጫ ቦርድ አካሄድ ገለልተኛ ላለመሆኑም ማሳያ ነው ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለውም ውሳኔው ከእነ አቶ ልደቱ አያሌው ጋር ያላቸውን የአብሮነት ጥምረት ለማዳከም ያለመ ቢሆንም  ትግላችን ግን አይቆምም ብለዋል አባይ ሚዲያ በውሳኔው ላይና ኢሃን ባቀረበው ቅሬታ ዙሪያ ተጫማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ለማነጋገር ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው ሊሳካ አልቻለም፡፡