አባይ ሚዲያ ግንቦት 08፤2012

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር ባለው የህግ ማእቀፍ መሰረት የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር ቤት አሳወቀች ባለ 22 ገፁ ደብዳቤ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ የተፈረመበት ሲሆን ለምክር ቤቱ ያስገቡት በUN የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ታዬ_አፅቀስላሴ መሆናቸው ታውቋል።

86 ፐርሰንቱ የናይል ውሃ የሚመነጨው ከሀገሬ ኢትዮጵያ ነው ብለው የሚጀምሩት አቶ ገዱ ግብፅ ግን በኮሎኒያል ስምምነት ላይ ተመስርታ የውሃውን የአንበሳ ድርሻ ስትጠቀም እንደኖረች ተናግረዋል በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ውሃውን አመንጭታ ለግብፅ ከማድረስ ባለፈ ለመጠቀም እንዳልቻለች ገልፀው ይህ ኢፍትሃዊነት ሊቀጥል አይችልም ብለዋል አቶ ገዱ።

65 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የማያገኝ ቢሆንም የግብፅ ህዝብ ግን ባጠቃላይ የአቅርቦት ሽፋን እንደሚያገኝ የሚጠቅሰው ደብዳቤው ግብፅ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ እንዳናገኝ እንቅፋት መሆኗን ኮንኗል ኢትዮጵያ ተጨማሪ የማሰቢያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት ገልፃ ባልተሳተፈችበትና በአሜሪካ አደራዳሪነት በተካሄደው የመጨረሻው ውይይት ላይ ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ውይይት መደረጉን አቶ ገዱ ለፀጥታው ምክር ቤት አሳውቀዋል።

አቶ ገዱ ግብፅ ቋሚ እንቅፋት መሆኗን አቁማ በትብብር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማድረግ ይገባታል ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት ለመጀመር ማሰቧ  ስምምነትንም ሆነ አለም አቀፍ የህግ ሃላፊነትን የጣሰ አይደለም ብለዋል ከአንድ ወር በፊት ጠ/ሚ አብይ ለአልሲሲና ለሱዳኑ ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ በላኩት ደብዳቤ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ስቴጅ ሙሌት በዚህ ክረምት እንደምትጀምር ቢያሳውቁም ግብፅም ሆነ ሱዳን አለመስማማታቸውን በደብዳቤ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የመጀመሪያ ስቴጅ ሙሌት ሁለት አመታት የሚወስድ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ እስከ 595 ሜትር ደረስ የግድቡን ቋት ለመሙላት ያስችላል ይህም ቋቱ 18.4 cubic meter እንዲይዝ የሚያስችል ሲሆን ይህ ውሃ የግድቡን ፓወር ፕላንት ለመሞከር ወይም ቴስት ለማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል።

በኢትዮጵያ በኩል በመጀመሪያው አመት 4.9 billion cubic meter በሁለተኛው አመት 13.5 cubic meter የውሃ ሙሌት ለማካሄድ ታስቧል ይህ ውሃ የሚወሰደው 49 cubic meter አመታዊ ፍሰት ካለው ብሉ ናይል ስለሆነ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ይህ ነው የሚባል ጉዳት አይኖረውም ሲልም ደብዳቤው ይገልፃል።

በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ሙሌቱን ለመጀመር የግብፅን ይሁንታ ማግኘት እንደማይጠበቅባት እና ህጋዊ ግዴታም እንደሌለባት አሳውቃለች ኢትዮጵያ ግብፅ ከዚህ በፊት ወደ ነበረው የሶስትዮሽ ውይይት እንድትመለስ የጠየቀች ሲሆን ይህ በተዘዋዋሪ በአሜሪካ መሪነት እየተካሄደ ባለው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ መቀጠል እንደማትሻ ጠቋሚ ነው ተብሏል።