አባይ ሚዲያ ግንቦት 11፤2012

በትግራይ ክልል ያሉ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች የመሰቦ ሲሚንቶ ማከፋፈል ስራ በአንድ አከባቢና በአንድ ኔትወርክ ነጋዴዎች በመያዙ ከ7 ወር በላይ ብራችን የከፈልንበት ሲሚንቶ ሊሰጠን አልቻለም” በማለት በትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በመገኘት ነው የተቃውሞ ድምፃቸውን ያሰሙት።

ነጋዴዎቹ በመስከረም ወር ከ300 ሽህ እስከ 700 ሽህ ብር አስቀድመው በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስገብተው ከ7 ወር በኋላ ስሚንቶ እንደሚያገኙ የተዋዋሉ ቢሆንም በውላቸው መሰረት አለመፈፀሙን ጠቅሰዋል ሲሉ የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አምዶም ገ/ስላሴ ተናግረዋል።

አቶ አምዶም እንደነገሩን ባለሀብቶቹ በአከባቢው የመጠቃቀም ኔትወርክ የተደራጁ የአንድ አከባቢ ዘመድ አዝማድ ብቻ እንዲያከፋፍሉ ተደርገዋል ሲሉ ተቃውሞ አቅርበዋል ነጋዴዎቹና ባለሃብቶቹ ሊያቀርቡ ካዘጋጇቸው ጥያቄዎች መካከል በፍትሀዊ መንገድ “እንደተራችን ይሰጠን ካልሆነ ደግሞ ብራችን መልሱልን” በማለት ተቃውሟቸውን ለዶ/ር ደብረፅዮን እናቀርባለን።” ማለታቸው ተሰምቷል።

አቶ አምዶም አክለውም የትግራይ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ለህወሓት በግልፅ ተቃውሞኣቸው ሲያሰሙ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው ሲሉ ለአባይ ሚዲያ ተናግረዋል ይህ ዜና በተጠናቀረበት ሰዓት ባለሀብቶቹ በክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ በር ተሰብስበው ዶ/ር ደብረፅዮንን እየጠበቁ መሆናቸውና ገና ምላሽ እንዳላገኙ አረጋግጠናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትላንት በስቲያ ግንቦት 9 ቀን 2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የክልሉ ፖሊስ በወጣቶች ላይ ተኩሶ 1 ወጣት በመግደሉና ሁለት ወጣቶች በማቁሰሉ ምክናየት በዛሬው ዕለት በአዲግራት ከተማ የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋብተዋል ተቃውሟቸውን የገለጹት ሰልፈኞች ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡