አባይ ሚዲያ ግንቦት 13፤2012

በሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባላት መካከል በተፈጠረ ግርግርና አባላት ስብሳባ ረግጠው በመውጣታቸው በተፈጠረ ውዝግብ የክልሉ ልዩ ሃይል እርምጃ መውሰዱን ለማወቅ ተችሏል የራጆ ሚዲያ ዘገባ እንደሚያመለክተውና የተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው የክልሉ ልዩ ሃይል በምክር ቤት አባላቱ ላይ በወሰደው እርምጃ በሰው ላይ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘገባው እንደሚያመለክተው 147 ከሚሆኑት የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባላት መካከል የተወሰኑት ተቃውሟቸውን በማሰማት የምክር ቤት ስብሰባውን ያቆሙ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ቢሮ ግቢ ውስጥ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ በልዩ ሀይል ፖሊስ አባላት ተበትነዋል፡፡

በተጨማሪም ልዩ ሀይሉ በወሰደው እርምጃ በአንዳንድ የምክር ቤት አባላት ላይ ጉዳት እንደደረሰና አብዛኞቹን ደግሞ ፖሊስ በጎዳናዎች ላይ ሲያሳድድ እንደነበር መረጃው ያመለክታል በሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በምክር ቤቱ ውስጥ በተፈጠረ ውዝግብና አለመግባባት  በርዕሰ መስተዳደሩ ላይ ከስልጣን የማንሳት ሙከራ ተደርጓል የሚል  መረጃ  መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን የዛሬውም ክስተት

ክልሉ ላይ ለተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ማሳያ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች ይገልጻሉ ዛሬ በተፈጠረው ችግር ስብሰባው ላይ ተቃውሞ ያሰሙት የምክር ቤት አባላት ትክክለኛው ምክናየት ግልጽ ባይደረግም ተቃውሟቸውን የገለጹት አባላት ግን በዋነኝነት የክልሉ ልዩ ሀይል የወሰደውን እርምጃ ኮንነዋል ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ በዛሬው ዕለት ስለተፈጠረው ችግር ከሶማሌ ክልል መንግስት በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡