አባይ ሚዲያ ግንቦት 18፤2012

ህወሓት አሁን ትግራይ ክልል ውስጥ ባለው መነሳሳት ስለደነገጠች በደሕንነት ክፍሏ በኩል ዋና ዋና የሚባሉ የተቃዋሚ መሪዎችን የመግደል ሐሳብ ላይ ተወያይታለች ሲሉ የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል አቶ አብረሃ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ የህወሓት ተቃዋሚዎች በመለየት እቅድ ወጥቷል ይላሉ፡፡

“የዐብይ አሕመድ መንግስት በሰብአዊ መብት ጥሰት ሰበብ የትግራይ ክልል መንግስትን በመወንጀል በክልላችን ጣልቃ ገብቶ ሊቆጣጠረን ስለፈለገ የህወሓት ተቃዋሚዎችን ለመግደል ፕላን አለው”ተብሎ በሰፊው እንዲሰራጭ፣ እንዲነገርና እንዲፃፍ የማድረግ እቅድ እንዳለው አቶ አብረሃ ያስረዳሉ በመሆኑም “ዐብይ እኛን ለማስወንጀልና ለመከፋፈል ፈልጎ የኛን ተቃዋሚዎች ለመግደል አቅዷል”

እየተባለ ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራና ህወሓት ተቃዋሚዎቿን እንደምትገድል ጽፈዋል ህወሃት ራሷ ገድላ “ይሄው ያልነው አልቀረም፤ እኛን ለማስወንጀል ዐብይ አስገዳላቸው” የሚል ውንጀላ በማቅረብ ህዝብን ለመቀስቀስና ተቃውሞን ለማስቆም ትፈልጋለች ብለዋል ሊቀመንበሩ መረጃውን ከነሱ ያገኘሁት ነው የሚሉት አቶ አብረሃ አቅዱንም የደሕንነት ክፍሉ ተወያይቶበት ለበላይ አካል ተልኳል ሲሉ ይገልሉ።

አቶ አብረሃ ደስታ ከትግራይ ክልል እንድወጣም ተነግሮኛል ግን አልወጣም የሚሉት አቶ አብረሃ ህወሓት አብርሃ ደስታ “በሌላ አካል ሊገደል ይችላል” ብላ ካሰበች ጋርድ ቀጥራ ትጠብቀኝ ካልሆነ ግን ከህወሓት ውጭ ማንም አይገድለኝም የሚል መልዕክትም አስፍራለች ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ምዕራብ ዞን የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች፡መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ 11 ቀናት አልፎባቸዋል።

ነዋሪዎቹ የዞኑ አተዳዳር እና የፀጥታ አካላት ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም የሚሉ ሲሆን ጥያቄያቸው ከክልሉ መንግሥት መልስ እስካላገኘ ድረስ ወደ ቤታቸው እንደማይመለሱ ይናገራሉ የማይ ሓንሰ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብርሃለይ ገብረእየሱስ “የወረዳው አስተዳዳሪዎች ለራሳቸው ወደ ሽረ እንዲቀርባቸው ክሳድ ጋባ ወረዳው ትሁን አሉ ህዝቡ ደግሞ የተሰጠንን ወረዳ የመሆን መብት ለምን እንከለከላለን በማለት ነው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄደ ያለው” በማለት ገልፀዋል።

ሌላኛዋ የማይሓንሰ ነዋሪ ወይዘሮ ለተብርሐን ደግሞ “ውሳኔው በጉቦ እና በሙስና በድብብቆሽ የተደረገ ነገር ነው” በሚል ነዋሪው ለተቃውሞ እንደተነሳ ይጠቅሳሉ የኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ ባለበት በዚህ ወቅት ለተቃውሞ መውጣታቸውን በሚመለከትም ሲናገሩ “ሕዝቡ ስለተቸገረ እንጂ ወዶ አይደለም ሞትም ቢሆን እንሙት። ፍትህ ማጣትም ሞት ነው፤ በኮሮና መሞትም ሞት ነው” ብለዋል።

የአስገደ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም አበራ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ወጣቶች ለሰባት ቀናት ያህል መንገድ ዘግተው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል  “የወረዳው ምክር ቤት የወሰነውን የማይቀበሉ ከሆነ የክልሉን ኃላፊዎች ማነጋገር እንዳለባቸው ገልጸንላቸዋል ቢሆንም ኃላፊዎች መጥተው ካላናገሩን እኛ ወደ ክልል አንሄድም ብለዋል” ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።