አባይ ሚዲያ ግንቦት 27፣ 2012

በሊባኖስ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ቀጣሪዎቻቸው ያሰናበቷቸው የኢትዮጵያ ሰራተኞች በሀገራቸው ቆንስላ ፊት ለፊት መሬት ላይ በብዛት አንድ ላይ ተኝተው የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭተዋል የሊባኖስ የሰራተኛ ሚኒስትር ሊሚያ የሚን ዱወይሂ ዛሬ ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ ፣ በሚኒስቴሩ አነሳሽነት ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ሆቴል መያዙን አስታውቀዋል ሲል የአረብኛው ሊባነን 24 ዘግቧል፡፡

የተፈጠረው ድርጊት አሳዛኝ መሆኑን በመጥቀስ ድርጊቱን ያወገዙት ሚኒስትሩ መንግስታቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት በሚፈጽሙ አሠሪዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ቃል መግባታቸውንም ዘገባው ያሳያል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የቤይሩት አውሮፕላን ማረፊያ እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች አውሮፕላን ማረፊያዎች ስራ ማቆማቸው ለችግር የተጋለጡ ሰራተኞችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ እድል በማጥበብ የሰራተኞቹን ቀውስ ይበልጥ እንዲባባስ ማድረጉም ተዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገሪቱ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በራሱ ወጪ ባለፉት ቀናት በሊባኖስ በችግር ላይ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት መመለሱ ይታወቃል በሊባኖስ ቤይሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ባለኝ ውስን አቅምና ጥቂት ሰራተኞች ዜጎችን ለመርዳት በርካታ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

ይሁንና ጽ/ቤቱ በፌስቡክ አድራሻው እንዳስታወቀው ተደራራቢ ስራዎች እና በአንድ አንድ ግለሰቦች የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ተግባራት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩበት ነው “ከሁሉም የሚያሳዝነው አንዳንድ ስርዓት- ዓልባ ግለሰቦች፤ ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች፣ ከህገ-ወጥ ግለሰቦችና የተደራጁ ኃይላት የገንዘብና መሰል ጥቅሞችን ለማግኘት ሲሉ ዜጎችን ለተለያዩ ችግሮች አሳልፈው በመስጠት ትልቅ አገራዊ ክህደት እየተፈጸ መሆኑ ነው፡፡

የተለያዩ የጥፋት ምክሮችን እየመከሩም ዜጎችን አደጋ ላይ እየጣሉ ይገኛሉ” ሲል ጽ/ቤቱ ለስራው ዋነኛ ፈተኛ የሆነበትን ጉዳይ ገልጿል በሊባኖስ ከ400 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገመታል ያለው ቆንስላ ጽ/ቤቱ ከ300 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እንደሆኑ ገልጿል በሊባኖስና በኢትዮጵያ መካከል የስራ ስምምነት የለም፡፡ “ይህ ሁሉ ህዝብም ወደ ሊባኖስ የገባው ያለ ስራ ስምምነት በህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በኩል ነው” ብሏል ጽ/ቤቱ፡፡

በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሊባኖሳውያን፣ ከሶሪያውያን፣ ከፍልስጤማውያን፣ ከግብጻውያን፣ ከሱዳናውያን እና ከሌሎችም ሀገራት ዜጎች ጋር ተጋብተው መዋለዳቸውንም የገለጸው ቆንስላው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በዚሁ ሀገር እንደሚኖሩ ጠቁሟል የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች ወደ ሀገራቸው መመለስ ሲፈልጉ እንዲመለሱ የማድረጉ ኃላፊነትም የአሰሪዎች ነው ያለው ጽ/ቤቱ የትራንስፖርታቸውንም ይሁን ሌሎች ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ እንዳለባቸውም ገልጿል፡፡

ይሁንና “በርካታ ሰራተኞች ፣ አሰሪዎች እና የሰው አዘዋዋሪዎች ያለባቸውን ኃላፊነት በመጣስ ቆንስላ ጽ/ቤቱ የትራንስፖርታቸውን እና ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ እንዲመልሳቸው በቆንስላው በመገኘት ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ” ብሏል ጽ/ቤት ለእነዚህና መሰል ችግሮችን የሊባኖስ መንግስት መፍት፡፡