አባይ ሚዲያ ግንቦት 30፤2012

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ ህወሐትን ታጥቆ እስከ መንቀሳቀስና ከአማፂ ቡድን ጋር ተቀላቀሎ እስከ መተኮስ በሚደርስ የጦር ተግባር ወንጅሏል ህወሓት የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን አስታጥቋል፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰው ኦነግ-ሸኔ ጋር ወግኖ ተዋግቷል እየተባለ የሚነገረውን መረጃም ሃሰት ነው ብሏል፡፡

አምነስቲ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት ለማድበስበስ የተደረገ ነው ያለው ፓርቲው “ያስታጠኩት ሰራዊት አለመኖሩ  የአደባባይ ሚስጥር ነው” ሲል  ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን በአባይ ማለዳ ዘግበን ነበር የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ከትግራይ ቴሌብዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓትን ከኦነግ ሸኖ አብሮ እየሰራ ነው፤ ለሚለው ህወሓት ልምድና አቅም ያለው ድርጅት ነው ብለዋል።

በትጥቅ ትግሉ ወቅት በአፍሪካ ስመጥር የነበረ መንግስት ማስወገድ የቻለ ድርጅት ሲሉም ፎክረዋል አቶ ጌታቸው ህወሃት አሁን ያለውን የፌደራል መንግስት በሀይል ማስወገድ አለብኝ ብሎ ካመነ እንደ ድሮ ጋራና ሽንተረሩ መሄድ ኣይጠበቅበትም ሲሉም ዛቻ መሰል ንግግር ሰንዝረዋል ሁሉንም ክልል አፈራርሰው ስለጨረሱ የመጨረሻ ፈልገው ያልተሳካላቸው ትግራይ ነው ያሉት አትፖ ጌታቸው ትግራይን የማተራመስ ፍላጎቱ ቆይተዋል ነገሩ ግን ሊሳካሊቸው ኣይችልም፣ የተደራጀ ህዝብ ነው ያለው በትግራይ ሲሉም በክልሉ ህዝብ እንደሚተማመኑ ገልጸዋል።

አራት ኪሎ ተሰብስቦ ሲሉ የገለጹት የፌደራል መንግስት ሃገርን በጠራራ ፀሓይ ለባዕድ ኣሳልፎ እየሸጠ ያለዉ አፍራሽ ቡድን እኮ አርአያዉና አማካሪዉ የገዛ ዜጎቹን ኩላሊታቸዉን ነጥቆ በኮንትሮባንድ ንግድ ተሰማርቶ ሃብት እያካበተ ያለዉ የአስመራዉ ኣምባገነን መንግስት ነዉ ሲሉም የኤርትራውን መንግስት ወቅሰዋል።”

ኦሮምያ ውስጥ ያለ ሰው እሽኮኮ ብሎ ስልጣን ላይ ካወጣ በኋላ ስራ ፍጠርልኝ ያለህን ወጣት፣ ቄሮ፣ ፎሌ የሚባለው፤ አይ ወያነ ስለነሳሳህ ነው ጥያቄ እያነሳህ ያለሀው ስትለው፣ ከዚህ የበለጠ ስድብ የለም አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ህዝብና በህወሓት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ያለው ቡድን፣ ፍላጎቱ ሊኖረው ይችላል። ፍላጎቱ ግን አቅምንም ጭምር እንደሚጠይቅ ማወቅ አለበት ብለዋል።

ህወሓትንና የትግራይን ህዝብ የማንበርከክ ፍላጎቱ ዛሬ የተፈጠረ ሳይሆን የዛሬ ሁለት ዓመት መጋቢት 24/2010 ዓ/ም ነው የተጀመረው ግን አቅሙ የለም ስለዚህ ፍላጎቱ አዲስ አይደለም፤ ፍላጎት ደግሞ አቅምን አይፈጥርም አራት ኪሎ ላይ ተሰባስቦ ሊመጡብኝ ነው በሚል ድንጋጤም አገር መፍረስ የለባትም ሲሉም የተለመደውን ትችትና ዘለፋ በፌደራል መንግስቱ ላይ ሰንዝረዋል።