አባይ ሚዲያ ሰኔ 01፤2012

ከሱዳን ጋር ወድማማች ህዝቦች ነን ያሉት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝብ ብዙ ችግሮችን አብረው አልፈዋል ከሱዳን ጋር ጦርነት አንሻም ግን “ሱዳን እና ኢትዮጵያን ለማዋጋት የሚፈልግ ኃይል የለም ማለት ግን አይቻልም” ብለዋልከሳምንታት በፊት በድንበር አካባቢ ተከሰተ ስለተባለው ችግርም ሁለቱ አገራት በሰላም ይፈቱታል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሰጥተዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ የአምነስቲን ሪፖርት በተመለከተ ደግሞ “የኢትዮጵያውያን መብት እየተጎዳ ነው ካለ ሪፖርቱ ፤ አይረባም ሳይሆን፤ የእኛም የጸዳ ተቋም ስላልሆነ ችግር ሊከሰት ይቻላል። እሱን ፈትሾ ማስተካከል ያስፈልጋል” በማለት ከሪፖርቱ ጋር የተለያዩ አላማዎች ቢኖሩም የሚስተካከለውን ለማረም ፈቃደኝነቱ እንዳለ ተናግረዋል።

“ካጠፋን መሸፈን አያስፈልግም፤ ስለዚህ መለስ ብሎ ለመፈተሽ ብዙ የሚያስጨንቀን ጉዳይ ግን አይደለም” ብለዋል የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ደግሞ ስድስት ዓመት በዘገየው ግድብ 6 ቢሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ማጣቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ ስምንት ኮንትራት 6 ተቋራጮች እንደሚሰሩት በመግለጽ አንዱ ተቋራጭ ከሥራ ቢዘገይ ለሌላው ተቋራጭ እንቅፋት እንደሚሆን ተናግረዋል።

የሕዳሴ ፕሮጀክት ከጥንስሱ ጀምሮ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ማጥናታቸውን እና በግድቡ ላይ ሜቴክ እንዲገባ መደረጉ ስህተት መሆኑን ተረድተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ ከለውጡ በኋላ ፕሮጅክቱ እንዴት እንደዳነ፤ “የምክር ቤት አባላት ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ “እጅግ የሚያኮሩ ኢትዮጵያዊያን” ያሏቸው ግለሰቦች አሁንም የሕዳሴ ገድብ ጉዳይ እየተደራደሩ እንደሚገኙም ጠ/ሚሩ አስታውሰዋል።

ምርጫን በተመለከተ ደግሞ ምርጫ ቦርድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫ ማድረግ አልችልም የሚለው ሪፖርት ሲደርሰኝ፤ “ከወ/ሪት ብርቱኳን ጋር ባልተለመደ መልኩ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገናል” በማለት ከምርጫ ቦርድ ውሳኔ ጋር ተስማምተው እንዳልነበረ ተናግረዋል ፓርቲያቸው ምርጫው እንዲካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ “ብልጽግና ምርጫ የሚያስፈራው ፓርቲ እንዳለሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው” ብለዋል።

ወ/ሪት ብርቱኳን፤ “እስካሁን ከነበረው በማንም መስፈርት የማያሳፍር ምርጫ ለማካሄድ ነው ኃላፊነት የተቀበልኩት። ከዚህ ውጪ የሆነ ምርጫ ይደረግ የሚሉ ከሆነ ሥራዬን እለቃለሁ። ምርጫ እንዲደረግ አታዙኝም ብለው ስልኩ ተዘጋ” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል።

ሌላው ጠ/ሚ ዐቢይ የተነሳላቸው ጉዳይ አሳሳቢው የእምቦጭ አረም ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የነበረው ማሽን ብዙ ውጤታማ እንደልነበረ እና 200 ሚሊዮን የሚፈጅ የተሻለ ማሽን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በተመለከተ ድግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ  በቻይና የሚገኝ አንድም ኢትዮጵያዊ ተማሪ በቫይረሱ አለመያዙንና ከቻይና ፕሬዝደንት ጋር መነጋገራቸውን እና ተማሪዎቹ ለከፋ ችግር ሳይጋለጡ ማለፋቸውን ተናግረዋል።