አባይ ሚዲያ ሰኔ 02፤2012

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 599 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቋል በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 336 መድረሱንም የሜና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ እድሜያቸው ከ1 እስከ 89 ዓመት የሆኑ 135 ወንዶችና 55 ሴቶች ናቸው ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 153 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል ናቸው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉንም ደክተር ሊያ በሪፖርታቸው አመላክተዋል ህይወታቸው ያለፈው አምስቱም ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ውስጥ እድሜያቸው 42 እና 40 ዓመት ወንዶች በህክምና ማእከል ህክምና ላይ የነበሩ እንዲሁም የ85 ዓመት እድሜ ያላቸው ሴት በጤኗ ተቋም ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆኑ፥ እድሜያቸው 32 ዓመት የሆነ ሴት እና 40 ዓመት የሆነ ወንድ በአስክሬናቸው ላይ በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ መሆኑን ገልፀዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 32 መድረሱን በመጥቀስ፤ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ፤ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ 18 ሰዎች (11 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከሶማሌ ክልል) ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 379 መድረሱንም አስታውቀዋል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ152 ሺህ 334 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 336 ደርሷል አሁን ላይ 1 ሺህ 923 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 32 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በተያያዘ መረጃ በአውሮፓ እና አውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህክምና ዶክተሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሀገር ቤት የሚደረገውን ጥረት መቀላቀላቸው ተገልጿል የህክምና ባለሞያዎቹ ባሉበት ሀገር ኮሮና የተገኘባቸውን ሰዎች በማከም የተሠማሩ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠላማዊት ዳዊት  ተናግረዋል።

ቫይረሱ የደረሰበትን ደረጃ እና የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለጤና ሚኒስቴር ብሎም ለሌሎች የመንግስት ተቋማት እየሰጡ ናቸው ብለዋል ሃኪሞቹ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሠዎች በማከም ተግባር ከተሰማሩ ኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸው ጋር በስራ አጋጣሚ ያገኟቸውን ልምዶች እንደሚለዋወጡም ተገልጿል።