አባይ ሚዲያ ሰኔ 07፤2012

ግብፃዊው ቢሊየነር ናጉኢብ ሳዊሪስ “ኢትዮጵያ ወደ ምክንያታዊነት ካልመጣች እኛ ግብፃውያን ጦርነት እናውጃለን” ብለው በትዊተር ገፃቸው ማስፈራቸው መነጋገሪያ ሆኗል የኦራስኮም ቴሌኮም እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶች ባለቤት ናጉኢብ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ አዲስ አበባ ተገኝተው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር።

ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ሊያፈስ አቅዶ የነበረውን 300 ሚልዮን ዶላር የዛሬ አራት አመት ገደማ ማዘግየቱም የሚታወስ ነው ያም አለ ይህ ግን በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ እንደገና የተጀመረው ድርድር ትናንትም ቀጥሎ ውሏል የትናንት ውሎውን ድርድር አስመልክቶ የኢፌዴሪ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንደገለጸው ኢትዮጵያ በድርድሩ ሁለት የቴክኒክና የህግ ቡድኖች ቢኖሩ በሚል ያቀረበችውን ሀሳብ ሱዳን ተቀብላለች።

ግብፅ ደግሞ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሳትቀበለው የቀረችውን ረዘም ያለ የድርቅ ጊዜን እና ደረቃማ ዓመትን በተመለከተ ዝርዝር ህግ መኖር አለበት የሚለውን ሃሳቧን በድጋሚ ማቅረቧን አስታውቋል በእለቱ በነበሩ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በተካሄደ ድርድር ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ባቀረበችው ሃስብ ላይ ንግግር መደረጉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በዚህም መሠረት የመጀመሪያው ዙር የግድቡን የውሃ አሞላል እና አሞላሉ የሚገዛበት መመሪያን በተመለከተ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ሃሳብ ለመቀጠል ከመግባባት መደረሱን አስታውቋል ረዥም ድርቅን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴ የውኃ አለቃቁ ላይ ህግ እንዲያዘጋጅ ኃላፊነት እንዲሰጠው እና ዝርዝር አለቃቀቅን በተመለከተ ግን ድርድር እንደሚያስፈልግ ከመግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል ሚኒስቴሩ።

የግድቡን ደህንነት የተመለከተም ህግ እና ግድቡ በሚኖረው አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ተፅእኖ ጥናት ማስፈለግ ላይ መግባባታቸውንም መግለጫው አመላክቷል የግብፅ ተደራዳሪዎች በእለቱ የነበራቸው ተሳትፎ የተቀዛቀዘ ነበር ያለው መግለጫው ከተራዘመ የድርቅ ሁኔታ ጋር ያላቸውን ፍላጎት በማሳወቁ ላይ ብቻ መሳተፋቸውን አመልክቷል።

ሆኖም በመጨረሻ ሰዓት የግብፅ ተደራዳሪዎች ውይይት ሲደረግበት በነበረው እና ከዚህ በፊት ራሳቸው ሊያሰራ የሚችል ሰነድ ነው ብለው አስተያየት የሰጡበትን ሱዳን ያቀረበችውን ሰነድ መልሰው ተቃውመዋል ብሏል ሚኒስቴሩ በተጨማሪም የራሳቸውን አቋም ይዘው እንዲቀርቡ መጠየቃቸውን የተቃወሙት ግብፃውያኑ ድርድሩ እየተካሄደ የግድቡ ውኃ ሙሌት ሊካሄድ አይገባም ሲሉም ተቃውመዋል።

እየተካደ ያለው ድርድር ሰኞ እንዲጠናቀቅ እና እስካሁን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያስቀመጧቸውን በድርድሩ የተገኙ ለውጦች እውቅና ላለመስጠት ፍላጎት ታይቶባቸዋል ብሏል መግለጫው ድርድሩ ቀጥሎ ሲካሄድም የእስካሁን ድርድሮችን መሠረት በማድረግ በተዘጋጁ መመሪያዎች እና ህጎች ላይ ሀሳብ እንደሚለዋወጡ ታውቋል ነገም በእስካሁኑ ድርድር የተገኙ ለውጦችን በመገምገም ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ድርድሩ እንደሚቀጥል መግለጫው አመልክቷል፡፡