አባይ ሚዲያ ሰኔ 08፤2012

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአት በ5636 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል በቫይረሱ ከተያዙት መካከል116ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው።

በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል እስካሁን 620 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም የቻሉ ሲሆን 60 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በዛሬው እለት 3 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሲሆን ሁለቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሲሆኑ አንዱ ደግሞ የአማራ ክልል ነዋሪ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታቋል፡፡

በዛሬው እለት አዲስ አባባ በ98 የኮሮና ተጠቂ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን አማራ ክልል ደግሞ 33 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት በማድረግ ከክልሎች ቀዳሚ ሆኗል፡፡