አባይ ሚዲያ ሰኔ 09፤2012

የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መስተዳደር መካከል ያለውን አለመግባባት በሽምግልና መፍትሔ እንዲያገኝ ለማገዝ ዛሬ ወደ መቀለ እንደሚሄዱ ተነግሯል የሽምግልና ቡድኑ ከመቀለ ጉዞው ባሻገር ለረጅም ጊዜ ግጭቶችና የሰላም መደፍረስ እንዳጋጠመው ወደሚነገርልት የምዕራብ ኦሮሚያ እካባቢዎች በመንቀሳቀስ ሰላም እንዲወርድ እንደሚጥር የቡድኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገልጸዋል ይህንንም ተከትሎ በርካታ አስታያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደዓ የሀገራቸዉ ጉዳይ የሚያሳስባቸዉ አባቶች ችግሮችን በእርቅ ለመፍታት ማሰባቸዉ ያስመሰግናል ያሉ ሲሆን  ከወያኔ ጋር የሚደረግ ሽምግልና ግን በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ወያኔ በአፉ እርቅ እያለ በእጁ ተንኮል ይሸርባል። በ2000 ዓም ዋዜማ ከቅንጅት ጋር የነበረዉ ታሪኩ ይህን ይመሠክራል የሚሉት የብልጽግናው አመራሩ ስለዚህ ቅድመ ሁኔታ ያስፈልጋል። ወያኔ እርቅ ከፈለገ የደበቃቸዉን ዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ለፌዴራሉ መንግስት ያሰረክባል የሚል ቅድመ ሁኔታም ያስቀምጣሉ።

ወያኔ በምርጫ ስም የኢትዮጵያን ህገ-መንግስት ለመናድ የሚያደርገዉን መፍጨርጨር ማቆም አለበት የሚሉት አቶ ታዬ ላለፉት 27 ዓመታት ዘርፎ ውጭ ሀገር ያከማቸዉን የሀገር ሀብት ቆጥሮ ማስመለስ አለበት፤ ይህ ከመሆኑ በፊት ስለሽምግልና ማዉራት ግን የኢትዮጵያዊያንን ቁስል ማመርቀዝ ይሆናል ሲሉም አስረድተዋል አቶ ታዬ አክለውም ፓርቲያቸው ብልፅግና  እስከ አሁን ጉዳዩን እንደማያዉቅ አሳውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ እየተካረረ በመሄድ ከኢህአዴግ መክሰም በኋላ የነበራቸው ግንኙነት ተቋርጦ አሁን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ይሰማል ይህ አለመግባባት ያሳሰባቸው የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሁለቱን ወገኖች ለማቀራረብ ዛሬ ማክሰኞ ወደ ትግራይ አቅንተዋል፡፡

የሽምግልና ቡድኑ ወደ መቀለ የሚሄድበት ዋና ዓላማ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መሄዱ እና ችግሩ እንዲፈታ ደግሞ መቀራረብና መነጋገር አስስፈካጊ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መስኡድ አደም ደግሞ ለቢቢሲ የሽምግልና ቡድኑ በሁለቱ ወገኖች ፖለቲካዊ አመለካከት የሚያነሳው ነገር እንደሌለ ጠቅሰው፤ መግባባትን በመፍጠር አገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት እንደሚጥሩ አመልክተዋል።

“እንደ ሐይማኖት አባትም እንደ አገር ሽማግሌም በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ እንላለን። ከዚያም በሚያደረጉ ውይይቶች ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ላይ መፍትሄዎች ይመጣሉ ብለን እናስባለን” ሲሉ ተናግረዋል በአገሪቱ የለውጥ እርምጃዎች መወሰድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በአንድ ግንባር ስር ለ25 ዓመታት በአንድ ላይ ሲሰሩ ከነበሩት ድርጅቶች ጋር የነበረው ትስስር ላልቶ ቅራኔ በአደባባይ ሲነገሩ ቆይተዋል በተለይም የአራት ክልላዊ ፓርቲዎች ጥምረት የነበረው ኢህአዴግ ከስሞ በብልጽንና ፓርቲ ሲተካና ህወሓት እራሱን ሲያገል ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተካረው አሁን ካለበት ደረጃ ላይ መድረሱ ይታወሳል።