አባይ ሚዲያ ሰኔ 10፤2012

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ገዢው መንግስት ሀላቂ የሆኑ ሀገራዊ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ እንደማይችል አስታውቋል የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለአባይ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት በመንግስት ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ እንዲያወጡ ገፊ  ምክናየት የሆናቸው በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተላለፉ ያሉ እንደ የደቡብ ክልልን በአዲስ መልክ የማዋቀር አይነት ዘላቂ ውሳኔዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ ናትናኤል የፌደሬሽን ም/ቤት የመንግስትን ስልጣን ማራዘሙን ይፋ ባደረገ ማግስት ገዢው መንግስት የደቡብ ክልልን እንደ አዲስ ለማዋቀር ምክረ ሀሳብ ማቅረቡና ወደ ትግበራ መግባቱ እንዳሳዘናቸው ነግረውናል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በህዝብ ይሁንታ የተመረጠና ቀጥተኛ ውክልና ያለው አይደለም ያሉ ሲሆን በዚህ አስገዳጅ የስልጣን መራዘም ወቅትም ዘላቂ የሆኑ ውሳኔዎችና ትግበራዎች መፈጸም እንደሌለባቸው ገልጸውልናል፡፡