አባይ ሚዲያ ሰኔ 13፤2012

በምስራቅ ጎጃም እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ ቀበሌ ብዛት ያላቸው የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው በመምጣት በፈፀሙት ጥቃት የአካባቢው ባለሀብት በሆኑት የአቶ ሽገዛ ጤናው መኖሪያ ቤትን አስከፍተው በመግባት እሮብ ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ አቶ ሽገዛ ጤናው እና ልጃቸውን ምስጋናው ሽገዛ በጥይት ገድለዋል፡፡

የሟች ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ጥሩ ደምስ ምን አልባት ገንዘብ አለው እንዝረፈው ብለው ይሆናል እንጂ ሌላማ ቢሆን ኖሮ ባለቤቴንና ልጄን ዝም ብለው ገለዋቸው አይሄዱም ነበር ሲሉ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ገልፀዋል የሟች ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ጥሩ ደምስ ሲቀጥሉም ልጅና ባለቤቴን ከመግደላቸው በተጨማሪም ሰሞኑን 100 ኩንታል ቦለቄ ሸጦ ሳጥን ውስጥ ያስቀመጠውን ገንዘብም ሳጥኑን በመስበር ዘርፈውት እንደሄዱ አስረድተዋል፡፡

የቀበሌውን ሊቀመንበር ጨምሮ ተኩሱን የሰሙ የአካባቢው አርሶ አደሮች ወደ ቦታው ቢመጡም አስቀድመው ቦታ በያዙት የልዩ ኃይል አባላት ታግተው ቆይተዋል የቀበሌው አመራር የሆኑትን ኮማንደር ምስጌን ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላውቅም የክልሉ ልዩ ሀይል ናቸው መተው ገለዋቸው የሄዱት ሲሉ ገልፀዋል በጉዳዩ ላይ ለአባይ ሚዲያ ማብራሪያ የሰጡት የወረዳው ልዩ ሀይል ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ምስጋናው ድርጊቱ መፈፀሙን አምነው ድርጊቱ የሚያስጠይቅ ከሆነም ተጠያቂ ነን ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ አዞቦ ወረዳ የመኾኒ ከተማ ፓሊስ ዋና ኣዛዥ ኮማንደር መሐሪ ገብረሃዋሪያ እንደገለፁት ትናንት አመሻሽ ላይ በራያ አዘቦ ወረዳ ”ሆረዳ” በተባለ ቦታ በመጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት የሁለት ወጣቶች ህይወት አልፏል እንደ አዛዡ ገለጻ የወጣቶቹ ህይወት ሊያልፍ የቻለው በወጣቶቹ መካከል የተፈጠረውን ጸብ ለመገላገል የገባ የአካባቢው ሚሊሻ በተኮሰው ጥይት በመመታታቸው ነው በወቅቱ ከሟቾቹ በተጨማሪ አንድ ሌላ ወጣት ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰበትም ኮማንደር መሃሪ ተናግረዋል።